🔇Unmute
አዲስ አበባ፤ የካቲት 30/2018 (ኢዜአ)፡- በአዲስ አበባ እና በሸገር ከተሞች ያለውን የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት አስተማማኝ ለማድረግ 4ኛው ምዕራፍ የዲስትሪቢዩሽን መስመር መልሶ ግንባታና ዐቅም ማሳደግ ፕሮጀክት እየተከናወነ ነው።
ሥራው እየተከናወነ የሚገኘው በ4 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር መሆኑን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የኮሙኒኬሽን ሥራ አስፈፃሚ አንዋር አብራር ለኢዜአ ገልጸዋል።
በዚህም መሠረት ሥራው 703 ኪሎ ሜትር የዲስትሪቢዩሽን ኔትዎርክ መልሶ ግንባታና ዐቅም ማሳደግን ያካተተ መሆኑን አመላክተዋል።
በተጨማሪም 2 ሺህ አዲስ የተለያየ ዐቅም ያላቸው ትራንስፎርመሮች ተከላና 2 ሺህ ነባር ትራንስፎርመሮችን ዐቅም የማሳደግ ሥራ የሚከናወንበት መሆኑን ጠቁመዋል።

በፕሮጀክቱ ከኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ ወጪ የሚሆኑ 56 ማሰራጫ መስመሮችን መልሶ የመገንባትና የማሻሻል እንዲሁም ከተፈቀደው የኃይል አጠቃቀም በላይ ሲሆን መቆጣጠር የሚያስችሉ 62 የሎድ ብሬክ ስዊች ገጠማ ይከናወናል ብለዋል፡፡
በአሁኑ ወቅት የፕሮጀክቱ አጠቃላይ የፊዚካል ሥራ አፈፃፀም 36 ነጥብ 74 በመቶ መድረሱን ጠቁመው፤ 2 ሺህ 857 የኮንክሪት ምሰሶዎች ተከላ ሥራም መከናወኑን አስታውቀዋል።

ሥራው ሲጠናቀቅ በአዲስ አበባና በሸገር ከተሞች በዓመት በ100 ኪ.ሜ የመካከለኛ የኃይል ማሰራጫ መስመር ላይ የሚከሰተውን የኃይል መቆራረጥ ድግግሞሽን በ27 በመቶ ለመቀነስ ያስችላል ነው ያሉት።
የትራንስፎርመር መቃጠልንም ወደ 2 በመቶ መቀነስ እንደሚያስችል አመላክተዋል።
ሀዋሳ፣ ነሐሴ20/2018 (ኢዜአ)፡-በሀዋሳ ከተማ የተጀመሩ የሐይቅ ዳርቻ እና የኮሪደር ልማት ሥራዎችን በተያዘላቸው ጊዜ ለማጠናቀቅ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን ...
Aug 27, 2026
ሐረሪ ፤ነሐሴ 7/2018 (ኢዜአ)፦በሐረሪ ክልል የኢንቨስትመንት ፍቃድ እና መሬት ወስደው ወደ ግንባታና ማምረት ባልገቡ 12 ባለሀብቶች ላይ የኢንቨስትመንት...
Aug 14, 2026
ደሴ፤ነሐሴ 6/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከ173 ሺህ ለሚበልጡ አርሶ አደሮች የሁለተኛ ደረጃ የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ደብተር መሰጠ...
Aug 13, 2026
ባሕር ዳር ፤ ሐምሌ 23/2018(ኢዜአ)፦በአማራ ክልል በሁሉም ዘርፎች በተከናወኑ ተግባራት የተሻለ የኢኮኖሚ እድገት ማስመዝገብ መቻሉን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር...
Jul 31, 2026