🔇Unmute
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 15/2018(ኢዜአ)፦ የቀብሪደሃር ዩኒቨርሲቲ በኢነርጂ ዘርፍ የሀገሪቱ የልህቀት ማዕከል ለመሆን የተሰጠውን ተልዕኮ ለማሳካት ወደ ተግባር መግባቱን የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ኢንጂነር አብዱልፈታህ ራቢ ገለጹ።
ኢነርጂ የአንድ ሀገር የኢኮኖሚ እና የማህበራዊ እድገት መሰረት ሲሆን በተለይም እንደ ኢትዮጵያ ባሉ በማደግ ላይ ያሉ ሀገራት የኢነርጂ አቅርቦት ከኢንዱስትሪ መስፋፋት፣ ከግብርና ዘመናዊነትና ከዜጎች የኑሮ ደረጃ መሻሻል ጋር ቀጥተኛ ቁርኝት አለው፡፡
በመሆኑም በኢነርጂ ዘርፍ እና በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መካከል ያለው ቁርኝት ለሀገር ኢኮኖሚ ዕድገትና ለቴክኖሎጂ ሽግግር ወሳኝ ተደርጎ የሚወሰድ ሲሆን ተቋማቱ የሀገርን የኢነርጂ ዘርፍ በማዘመን በኩል የማይተካ ሚና አላቸው፡፡
የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ኢንጂነር አብዱልፈታህ ራቢ ሀገራዊ ተልዕኮውን እውን ለማድረግ በዘርፉ ብቁ ባለሙያዎችን ለማፍራትና ምርምሮችን ለማካሄድ በቁርጠኝነት እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል።
በዚህም በተያዘው የትምህርት ዘመን በፔትሮሊየም ኢንጂነሪንግ የትምህርት ዘርፍ ማስተማር መጀመሩን ለአብነት ጠቅሰዋል።
በተጨማሪም ከኢነርጂ ዘርፍ ጋር የተያያዙ 27 የሁለተኛ ድግሪ እና 36 የመጀመሪያ ድግሪ ፕሮግራሞች ተከፍተው ስራ መጀመራቸውን አስታውቀዋል።
በዚህም በኢነርጂ ዘርፍ የሀገሪቱ የልህቀት ማዕከል ለመሆን የተሰጠውን ተልዕኮ በውጤታማነት ተግባራዊ በማድረግ ላይ እንደሚገኝ ጠቁመዋል፡፡
ተቋሙ የትምህርት ጥራቱን ለማሳደግና ዓለምአቀፍ ልምዶችን ለመቅሰም በዘርፉ ከፍተኛ ልምድ ካላቸው የቻይና ዩኒቨርሲቲዎች እና ሌሎች ዓለም አቀፍ ተቋማት ጋር በቅንጅት ለመስራት ዝግጅቱን ማጠናቀቁን ገልጸዋል።
ለሀገሪቱ የኢነርጂ ኢንዱስትሪ የሚመጥኑ፣ በዕውቀትና በክህሎት የበለጸጉ ባለሙያዎችን በማፍራት በኩል ዩኒቨርሲቲው ግንባር ቀደም ሚና እንደሚጫወት ፕሬዚዳንቱ አረጋግጠዋል።
ሀዋሳ፣ ነሐሴ20/2018 (ኢዜአ)፡-በሀዋሳ ከተማ የተጀመሩ የሐይቅ ዳርቻ እና የኮሪደር ልማት ሥራዎችን በተያዘላቸው ጊዜ ለማጠናቀቅ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን ...
Aug 27, 2026
ሐረሪ ፤ነሐሴ 7/2018 (ኢዜአ)፦በሐረሪ ክልል የኢንቨስትመንት ፍቃድ እና መሬት ወስደው ወደ ግንባታና ማምረት ባልገቡ 12 ባለሀብቶች ላይ የኢንቨስትመንት...
Aug 14, 2026
ደሴ፤ነሐሴ 6/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከ173 ሺህ ለሚበልጡ አርሶ አደሮች የሁለተኛ ደረጃ የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ደብተር መሰጠ...
Aug 13, 2026
ባሕር ዳር ፤ ሐምሌ 23/2018(ኢዜአ)፦በአማራ ክልል በሁሉም ዘርፎች በተከናወኑ ተግባራት የተሻለ የኢኮኖሚ እድገት ማስመዝገብ መቻሉን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር...
Jul 31, 2026