የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ማህበረሰብ እና ባህል

የክልሉን እምቅ የኢንዱስትሪ አቅም በተገቢው ለመጠቀም የተከናወኑ ተግባራት ውጤት ተገኝቶባቸዋል−ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ

Mar 25, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

ሀዋሳ ፤መጋቢት 15/2018 (ኢዜአ) ፡-የሲዳማ ክልልን እምቅ የኢንዱስትሪ አቅምና ምቹ ዕድል በተገቢው ለመጠቀም በጥናትና ምርምር ተደግፈው የተከናወኑ ተግባራት ውጤት እንደተገኘባቸው የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ ገለጹ።

"ለኢኮኖሚያዊ መዋቅራዊ ሽግግር ኢትዮጵያ ታምርት" በሚል መሪ ሐሳብ የተዘጋጀ የንቅናቄ መድረክ በሀዋሳ ከተማ እየተካሄደ ነው።


የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ በወቅቱ እንደገለጹት፤ የክልሉን እምቅ የኢንዱስትሪ አቅም በተገቢው ለመጠቀም የተከናወኑ ተግባራት ውጤት ተገኝቶባቸዋል።

በዚህም ኢንዱስትሪዎችን በተደራጀ መልኩ በመደገፍ ዘርፉ በማምረት አቅምና በስራ እድል ፈጠራ አቅሙን እንዲያጎለብት ማድረግ መቻሉን ተናግረዋል።

በክልሉ የሚንቀሳቀሱ ኢንዱስትሪዎችም ከአመራሩና ፋይናንስ ተቋማት ጋር በመቀናጀት ዘርፉ በሀገር ኢኮኖሚ ላይ የሚያበረክተውን አስተዋጽኦ ማሳደግ አለባቸው ብለዋል።

በዘርፉ የተጀመሩ ስራዎች ቀጣይነት እንዲኖራቸውም የክልሉ መንግስት ድጋፉን አጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል፡፡

ነዋሪዎች በኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ መነሻ በተዘጋጀ ኤግዚቢሽንና ባዛር ላይ ምርቶችን ከመሸመት ባለፈ የሀገር ውስጥ ምርትን የመጠቀም ልምድን እንዲያሳድጉም ጠይቀዋል።


የክልሉ ኢንደስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ አሻግሬ ጀምበሩ በበኩላቸው በክልሉ የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ከተጀመረ በኋላ የኢንዱስትሪዎች የማምረት አቅም መጨመሩን ገልጸዋል።

ወደ ውጭ የሚላኩ ምርቶች መጠን በመጨመር ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን በሀገር ውስጥ በመተካትም ኢኮኖሚያዊ አቅምን ማሳደግ ተችሏል ብለዋል።

የሀገር በቀል ኢኮኖሚ ሪፎርም አካል የሆነው የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ በክልሉ ከስራ ውጪ የነበሩ 80 ኢንዱስትሪዎች ወደ ስራ እንዲመለሱ እድል መፍጠሩንም ተናግረዋል።

በክልሉ በኢንዱስትሪው ዘርፍ እየተመዘገበ ያለውን ለውጥ ለማሳየት ከ160 በላይ ኢንዱስትሪዎች የተሳተፉበት ኤግዚቢሽንና ባዛር ዛሬ በይፋ እንደሚከፈትም ነው የተናገሩት።

በኤግዚቢሽንና ባዛሩም ከ60 ሚሊዮን ብር በላይ የገበያ ትስስር እንደሚፈጠር ጠቅሰው አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን የማስተዋወቅ እድል እንደሚፈጠርም ገልጸዋል።

በክልሉ ከ1 ሺህ 455 በላይ አነስተኛና መካከለኛ ኢንዱስትሪዎች መኖራቸውን ተናግረዋል።

በመድረኩም ከኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ በኋላ የተገኙ ውጤቶችና ቀጣይ አቅጣጫዎች ላይ ያተኮረ ሰነድ ቀርቦ ውይይት እየተደረገበት ነው።

"ለኢኮኖሚያዊ መዋቅራዊ ሽግግር ኢትዮጵያ ታምርት" በሚል መሪ ሐሳብ የተዘጋጀው ኤግዚቢሽንና ባዛርም በርእሰ መስተዳድሩ በይፋ እንደሚከፈትም ታውቋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በሀዋሳ የሐይቅ ዳርቻ እና የኮሪደር ልማት ሥራዎችን በተያዘው ጊዜ ለማጠናቀቅ ርብርብ እየተደረገ ነው-ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ

ሀዋሳ፣ ነሐሴ20/2018 (ኢዜአ)፡-በሀዋሳ ከተማ የተጀመሩ የሐይቅ ዳርቻ እና የኮሪደር ልማት ሥራዎችን በተያዘላቸው ጊዜ ለማጠናቀቅ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን ...

Aug 27, 2026

በሐረሪ ክልል የኢንቨስትመንት ፍቃድ እና መሬት ወስደው ወደ ግንባታና ማምረት ባልገቡ 12  ባለሀብቶች ላይ  እርምጃ ተወሰደ

ሐረሪ ፤ነሐሴ 7/2018 (ኢዜአ)፦በሐረሪ ክልል የኢንቨስትመንት ፍቃድ እና መሬት ወስደው ወደ ግንባታና ማምረት ባልገቡ 12 ባለሀብቶች ላይ የኢንቨስትመንት...

Aug 14, 2026

በአማራ ክልል ከ173 ሺህ ለሚበልጡ አርሶ አደሮች የሁለተኛ ደረጃ የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ደብተር ተሰጠ

ደሴ፤ነሐሴ 6/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከ173 ሺህ ለሚበልጡ አርሶ አደሮች የሁለተኛ ደረጃ የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ደብተር መሰጠ...

Aug 13, 2026

በክልሉ በሁሉም ዘርፎች በተከናወኑ ተግባራት የተሻለ የኢኮኖሚ እድገት ማስመዝገብ ተችሏል 

ባሕር ዳር ፤ ሐምሌ 23/2018(ኢዜአ)፦በአማራ ክልል በሁሉም ዘርፎች በተከናወኑ ተግባራት የተሻለ የኢኮኖሚ እድገት ማስመዝገብ መቻሉን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር...

Jul 31, 2026