የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ማህበረሰብ እና ባህል

የኢትዮጵያ የኮንስትራክሽንና ከተማ ልማት ፈጣን ዕድገት ሀገሪቱን አፍሪካዊት የብልፅግና ተምሳሌት የሚያደርጋት ነው-የትምጌታ አስራት (ዶ/ር)

Mar 26, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

አዲስ አበባ፤መጋቢት 16/2018 (ኢዜአ)፡-የኢትዮጵያ የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪና ከተማ ልማት ፈጣን ዕድገት ሀገሪቱን አፍሪካዊት የብልፅግና ተምሳሌት የሚያደርጋት መሆኑን የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስትር ዴኤታ የትምጌታ አስራት (ዶ/ር) ገለጹ።

የመጀመሪያው የኢትዮ-ጣሊያን የኮንስትራክሽን፣የመሰረተ ልማትና የከተማ ልማት ፎረም በአዲስ አበባ ተካሂዷል።


የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስትር ዴኤታ የትምጌታ አስራት (ዶ/ር) በዚህ ወቅት እንዳሉት፤ የ10 ዓመቱ የልማት ዕቅድ ኢትዮጵያን አፍሪካዊት የብልፅግና ተምሳሌት የሚያደርግ አመርቂ ውጤት እያስገኘ ነው።

ለአብነትም የሕዳሴ ግድብ ስኬት፣ አዲስ አበባን ጨምር ከ80 በላይ የከተሞች የኮሪደር ልማት ስኬቶች የኮንስትራክሽን ዘርፉን ፈጣን ዕድገት የሚያሳዩ መሆናቸውን ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪና የከተማ ልማት ፈጣን ዕድገትም ሀገሪቱን አፍሪካዊት የብልፅግና ተምሳሌት የሚያደርጋትን ተጨባጭ ለውጥ እያመጣ መሆኑን ተናግረዋል።

ባለፉት ሰባት ዓመታት በየዓመቱ ከስምንት ሺህ ኪሎ ሜትር በላይ አዳዲስ መንገዶችን በመገንባት እምርታዊ ለውጥ እያስመዘገበች መሆኗንም አንስተዋል።

በዚህም የኢትዮጵያ የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ የግልና የመንግስት ተቋማት በቢሊዬን ዶላር የሚገመት ዋጋ ያላቸው ፕሮጀክቶችን የሚያንቀሳቅሱበት ምህዳር መፈጠሩን ገልጸዋል።

የኢትዮ-ጣሊያን የኮንስትራክሽን፣መሰረተ ልማትና ኮንስትራክሽን ልማት ፎረም የሀገራቱን የድጋፍና ትብብር ወደላቀ ምዕራፍ ለማሸጋገር ወሳኝ መሆኑን ተናግረዋል።

የኢትዮ-ጣሊያን የዲፕሎማሲ ወዳጅነት የጣሊያን ኩባንያዎች በግንባታ ግብዓት፣ ማሽነሪና መሰል የንግድና ኢንቨስትመንት ዘርፍ የነቃ ተሳትፎ የሚያደርጉበትን ዕድል እንደፈጠረ አብራርተዋል።


በአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን የማክሮ ኢኮኖሚ ዘርፍ ዳይሬክተር ስቴፈን ካሪንጊ፤ የኢትዮ-ጣሊያን የመሰረተ ልማትና ከተማ ግንባታ ፎረም ሰፊ የኢኮኖሚ ሽግግር ለመፍጠር ያግዛል ብለዋል።

የኢትዮጵያ የኮንስትራክሽንና የመሰረተ ልማት ግንባታ ፈጣን ዕድገትም የአፍሪካ ከተሞች የብልፅግና ሞተር መሆናቸውን እንደሚያሳይ ገልጸዋል።

በአዲስ አበባ የመጣው እመርታዊ የከተሜነት ስኬትም ለአፍሪካ ከተሞች በተሞክሮነት የሚወሰድ መሆኑን ተናግረዋል።


በኢትዮጵያ የጣሊያን አምባሳደር ሴም ፋብሪዚ በበኩላቸው፣ የኢትዮጵያና ጣሊያን እረጅም ዘመናትን ያስቆጠረ የጋራ ርዕይና ትብብር ያላቸው ወዳጅ ሀገራት ናቸው ብለዋል።

የኢትዮ-ጣሊያን የኮንስትራክሽን፣ የመሰረተ ልማትና የከተማ ልማት ፎረምም የሀገራቱን ሁለንተናዊ ትብብር ወደላቀ ምዕራፍ በማሸጋገር ተጨማሪ አቅም እንደሚሆን ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

ሀዋሳን የቱሪዝም እና ኢንቨስትመንት ማዕከል የማድረግ ተግባራት ተጠናክረው ይቀጥላሉ

ሀዋሳ፤ ሰኔ 6/2018(ኢዜአ)፦ ሀዋሳ ከተማን በማልማት የቱሪዝምና የኢንቨስትመንት ማዕከልነቷን ይበልጥ ለማሳደግ የሚከናወኑ የልማት ተግባራት ተጠናክረው እንደሚ...

Jun 14, 2026

በጋምቤላ ክልል በዘንድሮው የመኸር እርሻ ለማልማት ከታቀደው ውስጥ 72 ከመቶ የሚሆነው መሬት በዘር ተሸፍኗል

ጋምቤላ፤ ሰኔ 3/2018(ኢዜአ)፦ በጋምቤላ ክልል በዘንድሮው የመኸር እርሻ ለማልማት ከታቀደው ውስጥ ከ72 በመቶ በላይ የሚሆነው መሬት በዘር መሸፈኑን የክልሉ ...

Jun 11, 2026

በዞኑ ከሰብል ልማት ጎን ለጎን በተከናወነ የንብ ማነብ ስራ ወደ 3 ሚሊዮን ኪሎ ግራም የሚጠጋ የማር ምርት ተገኘ

ደብረ ማርቆስ ፤ግንቦት 26/2018 (ኢዜአ)፦ በምስራቅ ጎጃም ዞን ከሰብል ልማት ጎን ለጎን በተከናወነ የንብ ማነብ ስራ ወደ 3 ሚሊዮን ኪሎ ግራም የሚጠጋ የማ...

Jun 4, 2026

በዲላ ከተማ የተዘጋጀው "ቡኖ - ማላ" ኤክስፖ ምርቶችንና የኢንቨስትመንት እድሎችን ለማስተዋወቅ አስችሏል

ዲላ፤ ግንቦት 16/2018 (ኢዜአ)፡-ከ40 በላይ የንግድ ተቋማትና አጋር አካላት ተሳትፈውበት በዲላ ከተማ የተዘጋጀው "ቡኖ - ማላ" ኤክስፖ ምርቶችን እና የኢ...

May 25, 2026