የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ማህበረሰብ እና ባህል

በኢንዱስትሪው ዘርፍ በተመዘገቡ ስኬቶች ለዜጎች በርካታ የስራ እድሎችን መፍጠር ተችሏል

Apr 1, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

አዲስ አበባ፤ መጋቢት 22/2018(ኢዜአ)፦ የለውጡ መንግሥት በኢንዱስትሪው ዘርፍ ያስመዘገባቸው ስኬቶች የስራ እድል ተጠቃሚ መሆን የሚችሉበትን ምቹ ሁኔታ እንደፈጠረላቸው በተለያዩ አምራች ኢንዱስትሪዎች የሚሰሩ ሙያተኞች ገለጹ።


ከለውጡ ወዲህ መንግሥት የኢንዱስትሪ ዘርፉን የሚያነቃቁ በርካታ ማሻሻያዎችን በማድረግ የኢንዱስትሪዎችን የማምረት አቅምንና ተኪ ምርትን የሚያሳድጉ፣ የሥራ ዕድል ፈጠራ እና ሌሎች ሰፋፊ ተግባራት ተከናውነዋል።


በዚህም ለሀገር ምጣኔ ሀብታዊ እድገት ጉልህ ድርሻ የሚጫወተውን የኢንዱስትሪ ዘርፉን ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ የፖሊሲ ለውጥን ጨምሮ የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄን በማስጀመር በዘርፉ እመርታዊ ለውጥ ማስመዝገብ ተችሏል።


በተከናወኑ ተግባራትም ሀገሪቱ ከውጭ የምታስገባቸውን ልዩ ልዩ ተኪ ምርቶች በሀገር ውስጥ ምርት የሚተካበትንና የውጭ ምንዛሬ የምታገኝበት ምቹ ምህዳር ተፈጥሯል።


በዚህም በአሁኑ ወቅት የኢንዱስትሪዎች አማካይ የማምርት አቅም 66 ነጥብ 3 በመቶ የደረሰ ሲሆን ይህም ለበርካታ ዜጎች የስራ እድል በመፍጠር የስራ አጥነትን ለመቅረፍ እንደ ሀገር የሚከናወኑ ስራዎች ውጤታማ እንዲሆኑ አወንታዊ አበርክቶ እያስገኘ ነው።


በተለያዩ አምራች ኢንዱስትሪዎች የስራ እድል ከተፈጠረላችው ወጣቶች መካከል ወጣት ሰኚ ገለታ ለኢዜአ እንደተናገረው ከከፍተኛ የትምህርት ተቋም በኢንዱስትሪያል ኬሚስትሪ በ2017 ዓ.ም መመረቁን አስታውሶ አሁን በዳቺ ማኑፋክቸሪንግ በምርት ተቆጣጣሪ ባለሙያነት እያገለገለ ይገኛል።


በድርጅቱ የስራ እድል ተጠቃሚ መሆኑ ከኢትዮጵያውያን ብሎም ከውጭ ባለሙያዎች በትምህርት የጨበጠውን እውቀት ይበልጥ የሚያሳድግበት ክህሎት እንዲያገኝ እንደረዳው ገልጿል።


በኬርመንት ጋርመንት የተለያዩ ስራዎችን በመስራት ላይ ያሉት ዓለም ሙላቱ በበኩላቸው፤ በኢንዱስትሪው በተፈጠረላቸው የስራ እድል ለበርካታ ዓመታት ሲሰሩ መቆየታቸውን ገልጸዋል።


በዘመኑ ታከለ እና ጓደኞቻቸው ሳሙና አምራች ሽርክና ማህበር የጥራት ቁጥጥር ባለሙያ የሆኑት ብሩክ አሰፋ በበኩላቸው፤ ዜጎች የስራ እድል ተጠቃሚነታቸውን ለማጠናከር በመንግስት በኩል የተጀመሩ ኢንዱስትሪዎችን የመደገፍ ስራ መጠናከር እንዳለበት ጠይቀዋል።


ወጣት እዮብ ደሬሳ በበኩሉ ከለውጡ ወዲህ በሀገሪቱ የኢንዱስሪዎች መጠናከርና መስፋፋት ከከፍተኛ ትምህርት ተመርቀው እንደወጡ በሙያቸው መስራት የሚችሉበትን የስራ እድል ተጠቃሚ እንዲሆኑ አስችሎኛል ብሏል።


የኢንዱስትሪ ሚኒስትር ዴኤታ ታረቀኝ ቡሉልታ የኢንዱስትሪ ዘርፉን ለማሳደግ አምራች የሰው ሀይል ወሳኝ ጉዳይ መሆኑን ተናግረዋል።


የኢንዱስትሪ ዘርፉን በሚፈለገው ደረጃ ለማሳደግ በዘርፉ ዜጎችን ማብቃት እንደሚገባ ጠቅሰው፤ በየዓመቱ በአማካኝ 350 ሺህ ዜጎችን የስራ እድል ተጠቃሚ ማድረግ እየተቻለ መሆኑን ተናግረዋል።


ሚኒስቴሩ የኢንዱስትሪው ዘርፍ የዜጎችን የስራ እድል ተጠቃሚነት ያረጋገጠ እንዲሆን ዘርፉ ላይ ያሉ ማነቆዎችን የመፍታት ስራ በልዩ ትኩረት እየተሰራ መሆኑን አረጋግጠዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

ሀዋሳን የቱሪዝም እና ኢንቨስትመንት ማዕከል የማድረግ ተግባራት ተጠናክረው ይቀጥላሉ

ሀዋሳ፤ ሰኔ 6/2018(ኢዜአ)፦ ሀዋሳ ከተማን በማልማት የቱሪዝምና የኢንቨስትመንት ማዕከልነቷን ይበልጥ ለማሳደግ የሚከናወኑ የልማት ተግባራት ተጠናክረው እንደሚ...

Jun 14, 2026

በጋምቤላ ክልል በዘንድሮው የመኸር እርሻ ለማልማት ከታቀደው ውስጥ 72 ከመቶ የሚሆነው መሬት በዘር ተሸፍኗል

ጋምቤላ፤ ሰኔ 3/2018(ኢዜአ)፦ በጋምቤላ ክልል በዘንድሮው የመኸር እርሻ ለማልማት ከታቀደው ውስጥ ከ72 በመቶ በላይ የሚሆነው መሬት በዘር መሸፈኑን የክልሉ ...

Jun 11, 2026

በዞኑ ከሰብል ልማት ጎን ለጎን በተከናወነ የንብ ማነብ ስራ ወደ 3 ሚሊዮን ኪሎ ግራም የሚጠጋ የማር ምርት ተገኘ

ደብረ ማርቆስ ፤ግንቦት 26/2018 (ኢዜአ)፦ በምስራቅ ጎጃም ዞን ከሰብል ልማት ጎን ለጎን በተከናወነ የንብ ማነብ ስራ ወደ 3 ሚሊዮን ኪሎ ግራም የሚጠጋ የማ...

Jun 4, 2026

በዲላ ከተማ የተዘጋጀው "ቡኖ - ማላ" ኤክስፖ ምርቶችንና የኢንቨስትመንት እድሎችን ለማስተዋወቅ አስችሏል

ዲላ፤ ግንቦት 16/2018 (ኢዜአ)፡-ከ40 በላይ የንግድ ተቋማትና አጋር አካላት ተሳትፈውበት በዲላ ከተማ የተዘጋጀው "ቡኖ - ማላ" ኤክስፖ ምርቶችን እና የኢ...

May 25, 2026