🔇Unmute
ድሬዳዋ፤ ሚያዝያ 9/2018 (ኢዜአ)፦በድሬዳዋ አስተዳደር ባለፉት ዘጠኝ ወራት ለህዝብ ተጠቃሚነት ልዩ ትኩረት በመስጠት ሰው ተኮር የልማት ስራዎች መከናወናቸውን የአስተዳደሩ ከንቲባ ከድር ጁሃር ተናገሩ።
ባለፉት ዘጠኝ ወራት ከ28 ሺህ ለሚበልጡ ዜጎች የስራ ዕድል እንደተፈጠረም ተገልጿል።
የድሬዳዋ አስተዳደር ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች የአስፈፃሚውን የበጀት ዓመቱን ዘጠኝ ወራት የስራ አፈፃፀም እና የመጪው በጀት ዓመት የትኩረት አቅጣጫዎች ላይ እየተወያዩ ነው።

የስራ አፈፃፀሙን ግምገማ እየመሩ የሚገኙት የአስተዳደሩ ከንቲባ ከድር ጁሃር በወቅቱ፤ ባለፉት ዘጠኝ ወራት ሰው ተኮር የልማት ስራዎችን በተቀናጀ መንገድ በማከናወን የህዝብን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ተችሏል ብለዋል።
በተለይም በስራ ዕድል ፈጠራ፣ ከተረጂነት ወደ ምርታማነት በማሸጋገር፣ በገጠርና በከተማ የመሠረተ ልማት ዝርጋታ፣ በኮሪደር ልማት እንዲሁም በአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፍ በአስተዳደሩ የተከናወኑ ተግባራት በአብነት የሚጠቀሱ ናቸው ብለዋል።
ባለፉት ዘጠኝ ወራት ከተረጂነት ወደ ምርታማነት ለመሸጋገር በተከናወኑ ስራዎችም 56 ሺህ የህብረተሰብ ክፍሎች ከልማታዊ ሴፍትኔት ፕሮግራም ሽግግር ማድረጋቸውን ጠቅሰዋል።
ሰብዓዊ ድጋፍን በራስ አቅም ለመሸፈን የተሰሩ ስራዎችም ውጤታማ መሆናቸውን አንስተው በአስተዳደሩ ገጠርና ከተማ ቀበሌዎች ዘመናዊ የእህል ማከማቻ መጋዘኖች ተገንብተው እህል መከማቸቱን አንስተዋል።
በተጨማሪም ከ45 ሚሊዮን ብር በላይ ለዚሁ ዓላማ ይውል ዘንድ መሰብሰቡን በማስታወስ።
እነዚህን ውጤታማ ስራዎች በበለጠ ለማሳደግ በቀጣይ ወራት ርብርቡ ይጠናከራል ብለዋል ከንቲባው።
የአስፈፃሚውን የዘጠኝ ወራት የስራ አፈፃፀም እና የ2019 በጀት ዓመት የትኩረት አቅጣጫዎች ለተወያዮች ያቀረቡት የአስተዳደሩ ፕላንና ኢኮኖሚ ልማት ኮሚሽን ኮሚሽነር ኃይለማሪያም ዳዲ ናቸው።

ኮሚሽነር ኃይለማሪያም እንዳሉት፤ ባለፉት ዘጠኝ ወራት ከ28 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ሰዎች ቋሚና ጊዜያዊ የስራ ዕድል በመፍጠር የወጣቶችን መሠረታዊ ጥያቄዎች መፍታት ተችሏል።
የስራ ዕድል ከተፈጠረላቸው መካከል 16 ሺህ የሚጠጉት በቋሚነት የስራ ዕድል ያገኙ መሆናቸውን አንስተዋል።
በተለይም ባለፉት ዘጠኝ ወራት የገጠርና የከተማውን ነዋሪዎች መሠረታዊ የልማት ጥያቄዎች በተጨባጭ የሚፈቱ 147 ነባርና አዳዲስ ፕሮጀክቶች በተሻለ አፈፃፀም ላይ መሆናቸውን ገልጸዋል።
ሀዋሳ፣ ነሐሴ20/2018 (ኢዜአ)፡-በሀዋሳ ከተማ የተጀመሩ የሐይቅ ዳርቻ እና የኮሪደር ልማት ሥራዎችን በተያዘላቸው ጊዜ ለማጠናቀቅ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን ...
Aug 27, 2026
ሐረሪ ፤ነሐሴ 7/2018 (ኢዜአ)፦በሐረሪ ክልል የኢንቨስትመንት ፍቃድ እና መሬት ወስደው ወደ ግንባታና ማምረት ባልገቡ 12 ባለሀብቶች ላይ የኢንቨስትመንት...
Aug 14, 2026
ደሴ፤ነሐሴ 6/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከ173 ሺህ ለሚበልጡ አርሶ አደሮች የሁለተኛ ደረጃ የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ደብተር መሰጠ...
Aug 13, 2026
ባሕር ዳር ፤ ሐምሌ 23/2018(ኢዜአ)፦በአማራ ክልል በሁሉም ዘርፎች በተከናወኑ ተግባራት የተሻለ የኢኮኖሚ እድገት ማስመዝገብ መቻሉን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር...
Jul 31, 2026