የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ማህበረሰብ እና ባህል

አገልግሎት አሰጣጥን ወደ ዲጂታልና ተንቀሳቃሽ አማራጮች በማሸጋገር የዜጎችን እርካታ ማሳደግ ለሀገራዊ ብልጽግና ዋነኛው መንገድ ነው

Apr 23, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 14/2018(ኢዜአ)፦ አገልግሎት አሰጣጥን ወደ ዲጂታልና ተንቀሳቃሽ አማራጮች በማሸጋገር የዜጎችን እርካታ ማሳደግ ለሀገራዊ ብልጽግና ዋነኛው መንገድ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ገለጹ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መሶብ የአንድ ማዕከል ተንቀሳቃሽ አገልግሎትን በይፋ ባስጀመሩበት ወቅት በኢትዮጵያ ለረጅም ዘመናት የቆዩ አገልግሎት የማግኘት ማነቆዎችን ለመፍታት በመንግስትም ሆነ በግል ዘርፍ ከፍተኛ የባህል ለውጥ ያስፈልጋል ብለዋል፡፡

አገልግሎት አሰጣጥን ወደ ዲጂታልና ተንቀሳቃሽ አማራጮች በማሸጋገር የዜጎችን እርካታ ማሳደግ ለሀገራዊ ብልጽግና ዋነኛው መንገድ መሆኑን ተናግረዋል፡፡


ባለፉት አስርት ዓመታት የተለያዩ መንግስታት የሲቪል ሰርቪስ ሪፎርም ለማድረግ ቢሞክሩም፣ አገልግሎቱን በሚፈለገው ልክ ማሻሻል እንዳልቻሉ አውስተዋል።

ለዚህም ዋናው ምክንያት ለረጅም ጊዜ የቆየውን ተቋማዊና ግለሰባዊ ባህል መቀየር፣ እጅ መንሻን ማስቀረትና ተገልጋይን አክብሮ የመሥራት ለውጥ ማምጣት ቀላል ባለመሆኑ ነው ሲሉ ገልጸዋል።

ከሀገራዊ ለውጡ ወዲህ ስትራቴጂ በመንደፍና ተቋማዊ ሥርዓት በመገንባት በአገልግሎት ዘርፉ እየተከናወነ ያለው ሪፎርም ተጨባጭ ውጤት እያመጣ መሆኑንም ተናግረዋል።

ግብርና፣ ኢንዱስትሪ፣ ቱሪዝም፣ ማዕድንና የዲጂታል የብዝኃ ዘርፍ የኢኮኖሚ ዕድገት ምሰሶዎችን ለማሳለጥ ቴክኖሎጂ ዋነኛው መሳሪያ መሆኑን ጠቁመዋል።

በዚህም በቴሌኮም፣ በፋይናንስና በሌሎች ዘርፎች ውጤት እየተመዘገበ እንደሚገኝ አንስተዋል።

መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ማዕከላት በአንድ ዓመት ውስጥ ወደ 45 ከፍ ማደጉን ጠቅሰው ከ100 በላይ ለማድረስ እየተሠራ መሆኑንም አስታውቀዋል።


ባለፈው አንድ ዓመት ከአንድ ሚሊየን በላይ ዜጎች በመሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎቶች ማግኘታቸውን ጠቅሰው፥ 3 ሺህ የሚጠጉ የአገልግሎት ዓይነቶች በአንድ ማዕከል እየተሰጡ ነው ብለዋል።

በሥራ ላይ ያሉት የመሶብ ማዕከላት ለኢትዮጵያ በቂ ባለመሆናቸው፣ አገልግሎቱን ወደ ህብረተሰቡ ይበልጥ ተደራሽ ለማድረግ መሶብ የአንድ ማዕከል ተንቀሳቃሽ የአውቶቡስ አገልግሎት መጀመሩን ጠቅሰዋል፡፡

አገልግሎቱን የሚሰጡ ተሽከርካሪዎች በኤሌክትሪክና በጋዝ የሚሠሩ፣ ኢንተርኔትና የተሟላ መሠረተ ልማት ያላቸው መሆናቸውን በማንሳት በአዲስ አበባና በክልሎች በስፋት ይሠራባቸዋል ነው ያሉት።

ይህ እርምጃ በአፍሪካ ፈር ቀዳጅ የሚባል የመንግስት እርምጃ መሆኑንም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጨምረው አክለዋል።

የአገልግሎት አሰጣጡ ከተንቀሳቃሽ ተሽከርካሪዎች ባለፈ ወደ ሞባይል ስልክ መሸጋገር እንዳለበት ጠቁመው ለዚህ ደግሞ የዲጂታል መታወቂያ ወሳኝ መሆኑን አስረድተዋል።

ማንኛውም ዜጋ ወደ መሶብ ማዕከል በመሄድ የአገልግሎት አሰጣጡን ለውጥ መመልከት እንደሚችል ገልጸውም፣ በሚቀጥሉት ሁለትና ሶስት ዓመታት ሰዎች ካሉበት ስፍራ ሆነው ሙሉ አገልግሎት የሚያገኙበትን ሥርዓት ለመዘርጋት ጥረት እየተደረገ መሆኑን አስታውቀዋል።

ከዚህ የሚገኘው ትሩፋት ለሀገር ዕድገት መዋል እንዳለበትም ነው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ያስገነዘቡት።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በክልሉ ምቹ የኢንቨስትመንት አካባቢ መፍጠር ዋነኛው የትኩረት አቅጣጫ ነው

ሀዋሳ ፤ሚያዝያ 14/2018 (ኢዜአ)፡-በሲዳማ ክልል ዘመናዊና ቀልጣፋ አሰራሮችን በመዘርጋት በርካታ አምራች ኢንዱስትሪዎችን ወደ ክልሉ በመሳብ የዜጎችን ተጠቃ...

Apr 23, 2026

በድሬዳዋ አስተዳደር አምራች ኢንዱስትሪዎች ተኪና ወጪ ምርቶችን የማምረት አቅማቸው ጨምሯል

ድሬዳዋ፤ ሚያዝያ 9/2018 (ኢዜአ)፦ በሀገራዊ ለውጡ ለአምራች ኢንዱስትሪዎች የተሰጠው ትኩረት በአስተዳደሩ የአምራች ኢንዱስትሪዎች ተኪና ወጪ ምርቶችን የማምረ...

Apr 17, 2026

የከተሞችን እድገትና የነዋሪዎችን ኑሮ ለማሻሻል ትኩረት ተሰጥቷል

ጅግጅጋ፣መጋቢት 22/2018 (ኢዜአ)፡- መንግሥት የከተሞችን እድገትና የነዋሪዎችን ኑሮ ለማሻሻል ትኩረት ሰጥቶ እየሠራ መሆኑ ተመለከተ። የኢትዮጵያ ከተሞች የ...

Apr 1, 2026

የኢትዮጵያ የኃይል አቅርቦት ስኬት ቀጣናዊ ትስስርን በማፋጠን የጋራ ብልፅግናን የሚያበስር የልማት አጀንዳ ነው

አዲስ አበባ፤ መጋቢት 16/2018(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ የኃይል አቅርቦት ስኬት ቀጣናዊ ትስስርን በማፋጠን የጋራ ብልፅግናን የሚያበስር አህጉራዊ የልማት አጀንዳ ...

Mar 26, 2026