የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ማህበረሰብ እና ባህል

ኢትዮጵያ በብሪክስ ማዕቀፍ ከተሳትፎ ባለፈ መፍትሄ አቅራቢ በመሆን ዘርፈ ብዙ ተግባራትን እያከናወነች ትገኛለች

Apr 23, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

ባህርዳር፤ሚያዝያ 14/2018 (ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ በብሪክስ ማዕቀፍ ከተሳትፎ ባለፈ መፍትሄ አቅራቢ በመሆን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነቷን ለማረጋገጥ ዘርፈ ብዙ ተግባራት እያከናወነች እንደምትገኝ የውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩት ገለፀ።

በባህር ዳር ከተማ ''የብሪክስ አሁናዊ አቅሞች እና የኢትዮጵያ የልማት ትብብር ትኩረቶች'' በሚል መሪ ሃሳብ የተዘጋጀው ጉባኤ መካሔድ ጀምሯል።

የኢንስቲትዩቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር መሐመድራፊዕ አባራያ በመድረኩ እንዳሉት፤ ኢትዮጵያ በብሪክስ አባልነቷ ንቁ ተሳትፎ እያደረገች ትገኛለች።

በዚህም ተሳትፎዋን በማሳደግ በጥናት ላይ የተመሰረቱ የተደራጁ የመፍትሔ ሀሳቦችን በማቅረብ ለኢትዮጵያ ብሎም ለአፍሪካ የሚጠቅሙ ተግባራትን እያከናወነች መሆኑን ገልፀዋል።

የብሪክስ ሚና እየጎላ መምጣቱን ጠቅሰው በዚህ ማዕቀፍ ውስጥ አለም አቀፋዊ አቅሞችን በማስተባበር እየገጠሙ የሚገኙ ችግሮች በትብብር መፍትሄ ያገኛሉ ብለዋል።

በማዕቀፉም ኢትዮጵያ የመፍትሄ ሀሳብ አፍላቂ በመሆን ዲፕሎማሲያዊ በሆነ መንገድ እየተሳተፈች እንደምትገኝ አመልክተዋል።

መድረኩ ኢትዮጵያ በኢኮኖሚ፣ በፈጠራና በቴክኖሎጂ እድገት ውስጥ የራሷን ድርሻ ለመወጣት የሚያስችላት የሁለትዮሽ ትብብር ጭምር የሚካሄድበት መሆኑንም አስረድተዋል።

የብሪክስ ማዕቀፋ በተለይም በግብርና እና ስንዴ ልማት፣ በአረንጓዴ ልማት፣ በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስና መሰል ዘርፎች ልምድ የሚሰጥበትና የሚገኝበት መድረክ መሆኑንም አንስተዋል።

በጉባኤው የኢትዮጵያ የ2025 የብሪክስ ተሳትፎ እና ቀጣይ አገራዊ ትኩረቶች፣ የኢትዮጵያ የአካዳሚክ ምርምርና አሰላሳይ ተቋማት ትኩረት ከሚደረግባቸው መስኮች ተጠቃሽ ናቸው ብለዋል።


በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የማህበራዊ ፖሊሲ ዋና አማካሪ አምባሳደር ሚኒልክ አለሙ በበኩላቸው፤ ኢትዮጵያ ከብሪክስ አባል ሀገራት አንዷ መሆኗ ቁልፍና መሰረታዊ ጉዳይ መሆኑን አመልክተዋል።

ብሪክስ የዓለምን ህዝብ 50 በመቶ፤ የዓለምን ኢኮኖሚ ደግሞ 40 በመቶ የሚሸፍን መሆኑን ጠቅሰው ከዚህ በመነሳት ኢትዮጵያ ሁለንተናዊ ተጠቃሚነቷን ታረጋግጣለች ነው ያሉት።

ብሪክስ የማይበገርና ዘላቂነት ያለው የትብብር ማእቀፍ መሆኑን ጠቅሰው፣ የኢትዮጵያን በባለብዙ ዘርፍ ዲፕሎማሲ በማሳተፍ ተጠቃሚነቷን ብሎም ተሰሚነቷን ያሳድጋል ብለዋል።

ይኸው ጉባኤ ለፖሊሲ አውጪዎችና ለሌሎች ጠቀሜታ የሚውል የመፍትሔ ሀሳብ ማፍለቂያ መድረክ በመሆኑ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባም አመላክተዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በሀዋሳ የሐይቅ ዳርቻ እና የኮሪደር ልማት ሥራዎችን በተያዘው ጊዜ ለማጠናቀቅ ርብርብ እየተደረገ ነው-ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ

ሀዋሳ፣ ነሐሴ20/2018 (ኢዜአ)፡-በሀዋሳ ከተማ የተጀመሩ የሐይቅ ዳርቻ እና የኮሪደር ልማት ሥራዎችን በተያዘላቸው ጊዜ ለማጠናቀቅ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን ...

Aug 27, 2026

በሐረሪ ክልል የኢንቨስትመንት ፍቃድ እና መሬት ወስደው ወደ ግንባታና ማምረት ባልገቡ 12  ባለሀብቶች ላይ  እርምጃ ተወሰደ

ሐረሪ ፤ነሐሴ 7/2018 (ኢዜአ)፦በሐረሪ ክልል የኢንቨስትመንት ፍቃድ እና መሬት ወስደው ወደ ግንባታና ማምረት ባልገቡ 12 ባለሀብቶች ላይ የኢንቨስትመንት...

Aug 14, 2026

በአማራ ክልል ከ173 ሺህ ለሚበልጡ አርሶ አደሮች የሁለተኛ ደረጃ የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ደብተር ተሰጠ

ደሴ፤ነሐሴ 6/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከ173 ሺህ ለሚበልጡ አርሶ አደሮች የሁለተኛ ደረጃ የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ደብተር መሰጠ...

Aug 13, 2026

በክልሉ በሁሉም ዘርፎች በተከናወኑ ተግባራት የተሻለ የኢኮኖሚ እድገት ማስመዝገብ ተችሏል 

ባሕር ዳር ፤ ሐምሌ 23/2018(ኢዜአ)፦በአማራ ክልል በሁሉም ዘርፎች በተከናወኑ ተግባራት የተሻለ የኢኮኖሚ እድገት ማስመዝገብ መቻሉን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር...

Jul 31, 2026