የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ማህበረሰብ እና ባህል

ለዜጎች በርካታ የሥራ ዕድል እየፈጠረ የሚገኘው አምራች ኢንዱስትሪ

Apr 24, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 16/2018 (ኢዜአ)፡- በአምራች ኢንዱስትሪዎች በተፈጠረላቸው የሥራ ዕድል ተጠቃሚ ከመሆናቸው ባሻገር ዕውቀትና ክኅሎታቸውን እያሳደጉ መሆኑን በተለያዩ ፋብሪካዎች የሥራ ዕድል የተፈጠረላቸው ወጣቶች ገለጹ፡፡

ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያው ትኩረት ከሰጣቸው ዋና ዋና ዘርፎች መካከል የአምራች ኢንዱስትሪውን ዐቅም ማሳደግ አንዱ ነው።


ይህም በዋናነት የውጭ ምርቶችን በሀገር ውስጥ በመተካት የውጭ ምንዛሪን ለማዳን ያለመ ነው።

ይህንን ተከትሎ በተከናወነው ተግባር ከዚህ ቀደም ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ ይወጣባቸው የነበሩ ምርቶች በሀገር ውስጥ እንዲመረቱ በማድረግ ረገድ ተጨባጭ ውጤቶች እየተመዘገቡ ይገኛሉ።

በተለይም ተኪ ምርቶችን በስፋት በማምረት ለሀገር ውስጥ ገበያ ከማቅረብ ባለፈ፤ ወደ ውጭ በመላክ ተጨማሪ የውጭ ምንዛሪ ከማግኘት አንጻር ከፍተኛ ውጤት እየተመዘገበ ይገኛል።

አምራች ኢንዱስትሪው ለወጣቶችና ለሴቶች ሰፊ የሥራ ዕድል እየፈጠረ ሲሆን፤ የቴክኖሎጂና የዕውቀት ሽግግር እንዲኖር በማድረግ የዜጎችን የኑሮ ደረጃ በማሻሻል ረገድ ከፍተኛ ሚና እየተጫወተም ይገኛል፡፡

ኢዜአ በተለያዩ ኢንዱስትሪዎች በመዘዋወር ያነጋገራቸው የሥራ ዕድል የተፈጠረላቸው ተጠቃሚዎች እንዳሉት፤ በተፈጠረላቸው የሥራ ዕድል ተጠቅመው ኑሯቸውን እየለወጡ ነው።


በጎበዝ ማኑፋክቸሪንግ ኤሌትሪክ ኢንዱስትሪ የምትሠራው ቅድስት አስማማው እንዳለቸው፤ በተፈጠረላት የሥራ ዕድል ገቢ ከማግኘቷ በተጨማሪ ክኅሎቷን እያሳደገላት ይገኛል።

ሌላኛው የሥራ ዕድል ተጠቃሚ ታምራት ተሰማ በበኩሉ፤ የአምራች ኢንዱስትሪዎች መስፋፋትን ተከትሎ የሥራ ዕድል ተጠቃሚ ከማድረጉ በተጨማሪ የዕውቀትና ቴክኖሎጂ ሽግግርን በማሳለጥ ረገድ ትልቅ ድርሻ እንዳለው ተናግሯል።


ይህንንም ተከትሎ ከዚህ በፊት በሌሎች ኢንዲስትሪዎች ከነበረው ልምድ አሁን ላይ በተሻለ ቴክኖሎጂ ራሱን ብቁ ማድረግ አንስቶ በፋብሪካው በሚከፈለው ክፍያ ራሱን ከማስተዳደር አልፎ ቤተሰብም እየደገፈ እንደሚገኝ ገልጿል፡፡

በዳቼ ማኑፋክቸሪንግ የምግብ ማቀነባበሪያ ፋብሪካ የሥራ ዕድል ተጠቃሚ የሆነው እዮብ ዱሬሳ በበኩሉ በድርጅቱ የሥራ ልምድ ማግኘት መቻሉን ገልጾ፤ በሚከፈለው ክፍያም ከራሱ አልፎ ቤተሰቦቹን መደገፍ መቻሉን ተናግሯል፡፡


በዚሁ ፋብሪካ በተፈጠረላት የሥራ ዕድል የኢኮኖሚ ተጠቃሚነቷ ማደግ እንደቻለ የገለጸችው ደግሞ ሌላኛዋ የሥራ ዕድል ተጠቃሚ አሚራ ጀማል ናት።


በሁዋጃን ልዩ ኢኮኖሚክ ዞን የጎበዝ የፀሐይ ኃይል ሶላር ሴል ማምረቻ ሥራ አስኪያጅ በረከት ኃይሉ፤ መንግሥት ለኢንዱስትሪ ዘርፉ በፈጠረው ምቹ ምኅዳር ምርታቸውን ለተለያዩ ሀገራት እየላኩ መሆኑን ተናግረዋል።


በመንግሥት እየተደረገ ያለው ድጋፍ የማምረት ዐቅማቸውን እንዳሳደገውም ገልጸዋል።

ድርጅቱ ከ600 በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የሥራ ዕድል መፍጠሩንም አስረድተዋል።

የዳቼ የምግብ ማቀነባበሪያ ፋብሪካ ፕላንት ማኔጀር ዐቢይ በቀለ በበኩላቸው፤ ለዘርፉ የተሰጠው ትኩረት ትልቅ ዕድል እየፈጠረላቸው መሆኑን ይናገራሉ፡፡


መንግሥት በየጊዜው በሚያደርግላቸው ድጋፍና ክትትል ምርቶቻቸውን በጥራትና በፍጥነት በማምረት ወደገበያ ተዳራሽ ለማድረግ እንዳስቻላቸውም አንስተዋል።

አሁን ላይ ድርጅቱ በአራት ፋብሪካዎች 46 ዓይነት የታሸጉ ምግቦችን እያመረተ ለሀገር ውስጥና ለውጭ ገበያ እያቀረበ መሆኑንም አረጋግጠዋል።

ፋብሪካው ሥራ ሲጀምር በ40 ሠራተኞች ብቻ መጀመሩን አውስተው፤ መንግሥት ለዘርፉ በሰጠው ትኩረትም ውጤታማ መሆን በመቻሉ አሁን ላይ ከ1 ሺ 300 በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የሥራ ዕድል መፍጠር መቻሉን ተናግረዋል፡፡

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በሀዋሳ የሐይቅ ዳርቻ እና የኮሪደር ልማት ሥራዎችን በተያዘው ጊዜ ለማጠናቀቅ ርብርብ እየተደረገ ነው-ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ

ሀዋሳ፣ ነሐሴ20/2018 (ኢዜአ)፡-በሀዋሳ ከተማ የተጀመሩ የሐይቅ ዳርቻ እና የኮሪደር ልማት ሥራዎችን በተያዘላቸው ጊዜ ለማጠናቀቅ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን ...

Aug 27, 2026

በሐረሪ ክልል የኢንቨስትመንት ፍቃድ እና መሬት ወስደው ወደ ግንባታና ማምረት ባልገቡ 12  ባለሀብቶች ላይ  እርምጃ ተወሰደ

ሐረሪ ፤ነሐሴ 7/2018 (ኢዜአ)፦በሐረሪ ክልል የኢንቨስትመንት ፍቃድ እና መሬት ወስደው ወደ ግንባታና ማምረት ባልገቡ 12 ባለሀብቶች ላይ የኢንቨስትመንት...

Aug 14, 2026

በአማራ ክልል ከ173 ሺህ ለሚበልጡ አርሶ አደሮች የሁለተኛ ደረጃ የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ደብተር ተሰጠ

ደሴ፤ነሐሴ 6/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከ173 ሺህ ለሚበልጡ አርሶ አደሮች የሁለተኛ ደረጃ የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ደብተር መሰጠ...

Aug 13, 2026

በክልሉ በሁሉም ዘርፎች በተከናወኑ ተግባራት የተሻለ የኢኮኖሚ እድገት ማስመዝገብ ተችሏል 

ባሕር ዳር ፤ ሐምሌ 23/2018(ኢዜአ)፦በአማራ ክልል በሁሉም ዘርፎች በተከናወኑ ተግባራት የተሻለ የኢኮኖሚ እድገት ማስመዝገብ መቻሉን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር...

Jul 31, 2026