አዲስ አበባ፤ ጥር 4/2017(ኢዜአ)፦ በሀረሪ ክልል በበጋ መስኖ 4 ሺ 700 ሄክታር ማሳ በአትክልት እና ፍራፍሬ ልማት መሸፈኑ ተገለፀ።
የበጋ መስኖ የአትክልት እና ፍራፍሬ ልማት ስራዎች የአርሶ አደሩን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥና የገበያ ዋጋን በማረጋጋት ከፍተኛ አበርክቶ እንደሚኖራቸው ተገልጿል።
የአርሶ አደሩን ምርታማነት ለማሳደግ ግብዓት ከማቅረብ ጀምሮ እየተደረገ ያለው የባለሙያ ድጋፍም ተጠናክሮ መቀጠሉን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።