
አዲስ አበባ፤ ጥር 30/2017(ኢዜአ)፦ በ26ኛው የዓለም እንስሳት ጤና የአፍሪካ አህጉራዊ ጉባኤ ላይ የተሳተፉ የዘርፉ ባለሙያዎች የእንስሳት ጤና ተቋማትንና የልማት ስራዎችን ጎብኝተዋል።
26ኛው የዓለም የእንስሳት ጤና ድርጅት የአፍሪካ አህጉራዊ ጉባኤ የእንስሳት ጤናን ማሻሻል በሚያስችሉ አጀንዳዎች ላይ ላለፉት ሶስት ቀናት በአዲስ አበባ ተከናውኖ ተጠናቋል፡፡
የጉባኤውን መጠናቀቅ ተከትሎም ተሳታፊዎቹ በኢትዮጵያ ያሉ የእንስሳት ጤናና የተለያዩ የልማት ስራዎችን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል፡፡

ጉብኝቱ በቢሾፍቱ ብሄራዊ የእንስሳት ጤና ኢንስቲትዩት፣ የአፍሪካ ህብረት የፓን አፍሪካ የእንስሳት ህክምና ክትባት ማዕከል/AU-PANVAC/ እና ኤልፎራ አግሮ ኢንዱስትሪን ያካተተ ሲሆን በአዲስ አበባ ደግሞ የአንድነት ፓርክን ተመልክተዋል፡፡
ተሳታፊዎቹ ብሄራዊ የእንስሳት ጤና ኢንስቲትዩትን በጎበኙበት ወቅት ኢንስቲትዩቱ ለእንስሳት በሽታዎች ክትባት ማምረትን፣ ልዩ ልዩ የእንስሳት መድኃኒቶች ማቀነባበርን፣ የክትባትና መድኃኒት ምርቶችን ለውጭ ገበያ ማቅረብና ሌሎች በሚሰራቸው ተያያዥ ስራዎች ላይ ገለጻ ተደርጎላቸዋል፡፡

በተጨማሪም መቀመጫውን በኢትዮጵያ ያደረገው የፓን አፍሪካ የእንስሳት ህክምና ክትባት ማዕከል/AU-PANVAC/ የደስታ በሽታን ለመከላከል ከተመሰረተበት ጊዜ ጀምሮ በአፍሪካ የእንስሳት ጤናን ለማሻሻል ጥራት ያለው ክትባትና ምርመራ መጠቀምን በማበረታታት ላይ እንደሚገኝ ማብራሪያ ተሰጥቷቸዋል፡፡
ከዚህ ጎን ለጎን በኢትዮጵያ እየተተገበረ ያለው የሌማት ትሩፋት ኢኒሼቲቭ ትኩረት ካደረገባቸው የእንስሳት ልማቶች አንዱ እንቁላልና ዶሮ ሲሆን ኤልፎራ አግሮ ኢንዱስትሪ እያከናወነ ያለውን የዶሮ እርባታን ጎብኝተዋል፡፡

በመስክ ምልከታው ሰፊና በርካታ የእንስሳት ጤናና ልማት ተሞክሮዎችን እንዲሁም ልምዶችን እንዳገኙ ተሳታፊዎቹ መናገራቸውን የግብርና ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡
ባሕርዳር፤ ጳግሜ 5/ 2018 (ኢዜአ) ፡-የሀገርን ቀጣይ ተስፋ እና የትውልዱን እጣ ፋንታ የተሻለ ለማድረግ የዛሬው ብርታትና ትጋታችን ወሳኝ ነው ሲሉ የአማራ ...
Sep 11, 2026
ወላይታ ሶዶ፤ ጳጉሜን 4/2018 (ኢዜአ) ፦በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ለዘመን መለወጫ በዓል የምርት አቅርቦት እጥረት እንዳይከሰት በቂ ዝግጅት መደረጉን የክልሉ ን...
Sep 10, 2026
ባህር ዳር፤ ጳጉሜን 1/2018 (ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የግብርናውን ዘርፍ ከአምራች ኢንዱስትሪው ጋር በማስተሳሰር ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ መቻሉን የክልሉ ...
Sep 7, 2026
ጋምቤላ፤ ነሐሴ 24/2018 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ለአሳ አጥማጆች የተደረገው የግብአት ድጋፍ አበረታች ውጤት እያስገኘ መሆኑን የክልሉ እንስሳትና ዓሳ ሃ...
Aug 31, 2026