የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ

<p>በኦሮሚያ ክልል የእደ ጥበብ ማዕከላትን ከሥራ ዕድል መፍጠሪያነት ባለፈ የቱሪዝም ምንጭ ለማድረግ እየተሰራ ነው - የክልሉ ቱሪዝም ኮሚሽን</p>

Feb 10, 2025

IDOPRESS

አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- በኦሮሚያ ክልል የእደ ጥበብ ማዕከላትን ከሥራ ዕድል መፍጠሪያነት ባለፈ የቱሪዝም ምንጭ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን የክልሉ ቱሪዝም ኮሚሽን ገልጿል።

የኦሮሚያ ቱሪዝም ኮሚሽን ኮሚሽነር ለሊሴ ዱጋ እና ሌሎች የሥራ ሀላፊዎች በሸገር ከተማ ለገጣፎ ለገዳዲ ክፍለ ከተማ የክህሎት ማጎልበቻ ማዕከልን ጎብኝተዋል።


ኮሚሽነር ላሊሴ ዱጋ ጉብኝቱ ላይ እንደተናገሩት የእደ ጥበብ ሥራ ለወጣቶች የሥራ ዕድል ከመፍጠር በሻገር ለቱሪዝም ገበያ ትልቅ አቅም ነው።

በተለይም የባህል አልባሳትን ጨምሮ ሌሎች የእደ ጥበብ ውጤቶች ተጨማሪ የቱሪስት መስህብ በመሆናቸው በዘርፉ ለተሰማሩትም ገቢ ይፈጥራሉ ብለዋል።

ኮሚሽኑ በክልሉ በተለያዩ አካባቢዎች የሚታወቁ የእደ ጥበብ ውጤቶች የሥራ ዕድል ከመፍጠር ባለፈ የቱሪዝም አቅም እንዲሆኑ የበኩሉን ድጋፍ ያደርጋል ብለዋል።

በሸገር ከተማ ለገጣፎ ለገዳዲ ክፍለ ከተማ አስተዳዳሪ አቶ ጫላ አዳሬ በበኩላቸው በክፍለ ከተማው በርካታ የእደ ጥበብ ማምረቻ ማዕከላት እንዳሉ ጠቅሰዋል።

እነዚህ ማዕከላት ለወጣቶች የሥራ ዕድል መፍጠሪያ እንዲሆኑ ስልጠናን ጭምሮ በተለያየ መልኩ ድጋፍ እየተደረገ መሆኑን አመልክተዋል።


በክፍለ ከተማው የሚገኘው ጉዲና ቱምሳ ፋውንዴሽን የወጣቶች ሙያ ማጎልበቻ ማሰልጠኛ ማዕከል ዳይሬክተር ወይዘሮ ሌንሳ ጉዲና ማዕከሉ ወጣቶችን በማደራጀት በሚፈልጉት የእደ ጥበብ የሙያ መስክ በማሰልጠን ሰርተው እንዲጠቀሙ እያደረገ መሆኑን ተናግረዋል።

ማዕከሉ በሦስት ዓመት ጊዜ ውስጥ ከ2 ሺህ በላይ ወጣቶችን በተለያዩ ሙያዎች በማሰልጠን የሥራ ዕድል ተጠቃሚ ለማድረግ አቅዶ እየሰራ መሆኑንም ገልጸዋል።

ማዕከሉ በዋናነት ወጣቶችን በሸማ፣ በሸክላና በሌሎች የእደ ጥበብ ሥራዎች እያሰለጠነ መሆኑንም ተናግረዋል።

በማዕከሉ ስልጠና ያገኙ ወጣቶችም በስልጠናው ባገኙት ክህሎት የሥራ ዕድል እንደተፈጠረላቸው አንስተዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.