አዲስ አበባ፤ የካቲት 10/2017(ኢዜአ)፦በሀረር ከተማ የሚከናወነው land mark የኮሪደር ልማት ስራ በጥራትና በፍጥነት እንዲጠናቀቅ ሁሉም የድርሻውን ሊወጣ ይገባል ሲሉ የክልሉ ርእሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ ገለጹ።
በከተማው ከስታዲየም እስከ ሐረር በር የሚሰራው land mark የኮሪደር ልማት ስራ መጀመሩን ርዕሰ መስተዳድሩ ተናግረዋል።
ኮሪደሩ በተሻለ ጥራትና ባጠረ ጊዜ እንዲከናወን ሁላችንም የድርሻችንን እንድንወጣ ጥሪዬን አቀርባለሁ ማለታቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ጽሕፈት ቤት መረጃ ያሳያል።