አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ አዲሱ የዓለም የፉክክር መድረክ እየሆነ መጥቷል።
በልብወለድ ወይም በምናብ የሚታሰቡ ፈጠራዎች፤ በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ እውን እየሆኑም ይገኛሉ።
እ.ኤ.አ ከ2012 ወዲህ በከፍተኛ ደረጃ ዕድገት ያሳየው አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ በአሁኑ ጊዜ ከሰዎች የቀን ተቀን ሕይወት ጋር እየተዛመደ መጥቷል።
በዕለት ተዕለት የሰዎች እንቅስቃሴ ውስጥ ከፍተኛ ጠቀሜታ ያላቸውን የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ መጠቀሚያዎች እንመልከት።
👉ቻት ጂፒቲ (ChatGPT): ጥያቄዎችን ለመመለስ፣ ሀሳቦችን ለማመንጨት እንዲሁም በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ መረጃዎችን ለማግኘት የሚረዳ ነው።
👉ግራመርሊይ (Grammarly) : በፅሁፍ ውስጥ የግራመር (ሰዋሰው) እንዲሁም የስርዓተ ነጥብ ስህተቶች የሚያርም የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ መጠቀሚያ ነው።
👉ካንቫ (Canva) : የተለያዩ ግራፊክስ ስራዎችን በቀላሉ የሚሰራልን መጠቀሚያ ነው።
👉ኦተር ኤአይ (Otter.ai) : በድምፅ የምንናገራቸውን ወደ ፅሁፍ (text) የሚቀይር መጠቀሚያ ሲሆን በአብዛኛው በትምህርት ቤት ውስጥ ለሌክቸር ይጠቀሙታል::
👉ክራዮን (Craiyon) : ፅሁፍ ብቻ በመፃፍ የምንፈልገውን ፎቶ ለመፍጠር የሚረዳ መጠቀሚያ ነው።
👉ሬፕሊካ (Replica) : የኤ አይ ቻት ቦት ሲሆን ስለ አዕምሮ ህክምና የሚያማክር እንዲሁም የግል የአዕምሮ ህክምና ምክር የሚሰጥ ነው።
👉ማይክሮሶፍት ቱ ዱ (Microsoft To Do): የቀን ሥራዎቻችንን ለማቀድ እና ለማደራጀት የሚያግዝ የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ መጠቀሚያ ነው።
👉ሄሚንግዌይ ኤዲተር (Hemingway Editor): የኦንላይን መፃፊያ ሲሆን አፃፃፋችን የጠራ እና ሀሳብን የያዘ እንዲሆን የሚያግዝ መጠቀሚያ ነው።
👉ጎግል አሲስታንት (Google Assistant): የቨርቹዋል አጋዥ መጠቀሚያ ሲሆን የቤት ውስጥ ስማርት መሳሪያዎችን ለመቆጣጠር፣ ጥያቄዎችን ለመመለስ እንዲሁም አስታዋሽ በመሆን ያገለግላል።
👉ጎግል ፎቶ (Google Photos): ፎቶዎችን ለማደራጀት እንዲሁም ለመፈለግ የሚረዳ የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ መጠቀሚያ ነው።