
አሶሳ የካቲት 16/2017 (ኢዜአ) ፡- በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የልማትና የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በመፍታት የተገኙ ስኬቶችን ማስቀጠል ይገባል ሲሉ በአሶሳ ከተማ በተካሄደው የህዝብ ኮንፍረንስ የተሳተፉ የህብረተሰብ ክፍሎች ተናገሩ።
በአሶሳ ከተማ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የተሳተፉበት አገር አቀፍ የህዝብ ኮንፍረንስ ተካሂዷል።

በኮንፍረንሱ ላይ አስተያየታቸውን ከሰጡት ነዋሪዎች መካከል አቶ ራህመተላ ታጀሲር፤ በአካባቢው የነበረውን የፀጥታ ችግር የክልሉ መንግስት ከህብረተሰቡ ጋር የፈታበት መንገድ የሚበረታታ ነው።
''የክልሉ መንግሥት ለጀመራቸው የልማት ሥራዎች አጋርነታችንን እንቀጥላለን'' ያሉት አስተያየት ሰጪ የተጀመሩ መልካም ስራዎች መጠናከር አለባቸው ብለዋል።
በቀጣይ በክልሉ የኤሌክትሪክ አገልግሎት እንዲሁም ትራንስፖርት አገልግሎት ተደራሽነት ላይ በትኩረት መስራት እንደሚገባም አንስተዋል።

ወይዘሮ ነበሩ ጨርቆሴ በበኩላቸው መንግስት ያመጣቸው የልማት ኢንሼቲቮች በመተግበር ላይ መሆናቸውን ገልጸው፤ ይኸም ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ብለዋል።
ከአጎራባች ኦሮሚያ እና አማራ ክልሎች ጋር ያለውን አብሮነት በማጠናከር በክልሉ የተገኘውን ሰላም ማስቀጠል እንደሚገባ የተናገሩት ደግሞ የሀገር ሽማግሌው ሼህ ኢብራሂም ሲራጅ ናቸው።

የአሶሳ ከተማ የስታዲየም ግንባታን ጨምሮ የተጀመሩ የልማት ፕሮጀክቶችን በማጠናቀቅ ለአገልግሎት ክፍት ማድረግ እንደሚገባም አስተያየት ሰጪዎቹ ተናግረዋል።
ህዝባዊ ኮንፍረንሱን የመሩት የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል፤ ለውጡ አዳዲስ ድሎች እንዲመዘገቡ ያደረገ ነው ብለዋል።

ህብረተሰቡ የሚያነሳቸው የልማት እና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን ለመመለስ እየተሰራ መሆኑንም ጠቁመዋል።
የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሀገሪቱን የኢኮኖሚ አቅምን የሚያጠናክር ክልል መሆኑን የገለፁት ሚኒስትሯ፤ ይህም ለክልሉ ህዝብ መልካም አጋጣሚ እንደሆነ አክለዋል።
በብልጽግና ፓርቲ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ኢሳቅ አብዱልቃድር በበኩላቸው የተነሱ አስተያየቶች ትክክለኛ እና በፓርቲው አቅጣጫዎች ላይ የተቀመጡ ናቸው ብለዋል።

ለልማትና መልካም አስተዳደር ችግሮች ምላሽ ለመስጠት የተያዙት ውሳኔዎችና አቅጣጫዎች የብልጽግና ጉዞ የሚያሳኩ መሆናቸውንም አረጋግጠዋል።
በመድረኩ ላይ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ተወካዮች ተሳትፈዋል።
ባሕርዳር፤ ጳግሜ 5/ 2018 (ኢዜአ) ፡-የሀገርን ቀጣይ ተስፋ እና የትውልዱን እጣ ፋንታ የተሻለ ለማድረግ የዛሬው ብርታትና ትጋታችን ወሳኝ ነው ሲሉ የአማራ ...
Sep 11, 2026
ወላይታ ሶዶ፤ ጳጉሜን 4/2018 (ኢዜአ) ፦በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ለዘመን መለወጫ በዓል የምርት አቅርቦት እጥረት እንዳይከሰት በቂ ዝግጅት መደረጉን የክልሉ ን...
Sep 10, 2026
ባህር ዳር፤ ጳጉሜን 1/2018 (ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የግብርናውን ዘርፍ ከአምራች ኢንዱስትሪው ጋር በማስተሳሰር ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ መቻሉን የክልሉ ...
Sep 7, 2026
ጋምቤላ፤ ነሐሴ 24/2018 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ለአሳ አጥማጆች የተደረገው የግብአት ድጋፍ አበረታች ውጤት እያስገኘ መሆኑን የክልሉ እንስሳትና ዓሳ ሃ...
Aug 31, 2026