የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ልዩ ዘገባ

<p>ኮርፖሬሽኑ ለቤቶች ልማት የሚያስፈልገውን የፋይናንስ ሀብት ምንጭ ማስፋት ላይ በትኩረት እንደሚሰራ ገለጸ</p>

Feb 26, 2025

IDOPRESS

አዲስ አበባ ፤ የካቲት 18/2017(ኢዜአ)፦ የፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን የመንግስት እና የግል አጋርነትን መፍጠርን ጨምሮ ለቤቶች ልማት የሚያስፈልገውን አማራጭ የፋይናንስ ምንጮች በጥናት መለየቱን አስታወቀ።

በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲግንስ ስር ያሉ ተቋማት የግማሽ ዓመት የስራ አፈጻጸም ግምገማ መካሄዱን እንደቀጠለ ነው።

የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን የስድስት ወራት አፈጻጸም ቀርቦ ግምግማ ተደርጎበታል።

ኮርፖሬሽኑ በገቢ አሰባሰብ፣ በቤት አቅርቦት፣ የቤቶች ጥገና እና ለግንባታዎች አስፈላጊውን ፋይናንስ በመመደብ ረገድ የላቀ አፈጻጸም ማስመዘገቡ ተመላክቷል።

በግምገማው እንደቀረበው ኮርፖሬሽኑ አፈጻጸሙን ይበልጥ ለማላቅ የንብረት እና ሀብት አስተዳደር አቅሙን ለማሳደግ እቅድ ይዟል።

ለዚህም የኪራይ ሊዝ ስምምነቶች እና የውል አስተዳደር ላይ ትኩረቱን አድርጎ እንደሚሰራ ገልጿል።

በተጨማሪም ኮርፖሬሽኑ በቀጣይ ስድስት ወራት ትኩረት የሚያደርግባቸው የስትራተጂ ትኩረት አቅጣጫዎችንም ለይቷል።

በሪል ስቴቶች ውስጥ ገቢ አመንጪ የሆኑ ንብረቶችን በባለቤትነት መያዝ እና ማስተዳደር፣ የመንግስት እና የግል አጋርነት እንዲሁም ሽርክናን ጨምሮ ለቤቶች ልማት የሚያስፈልጉ አማራጭ የፋይናንስ ሀብቶችን ማፈላለግ ላይ በትኩረት ለመስራት ማቀዱን ከኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲግንስ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.