የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ

<p>በአማራ ክልል የሚገኙ ኢንዱስትሪዎች ተኪ ምርት በማምረት በኩል አበረታች ውጤት እያስመዘገቡ ነው</p>

Feb 27, 2025

IDOPRESS

ደብረ ብረሀን፤ የካቲት 19/2017(ኢዜአ)፡- በአማራ ክልል የሚገኙ ኢንዱስትሪዎች ተኪ ምርቶችን በማምረት በኩል አበረታች ውጤት እያስመዘገቡ መሆኑን የክልሉ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ሃላፊ አቶ እንዲሪስ አብዱ ገለጹ።

ቢሮው በበጀት ዓመቱ እቅድ አፈጻጸም ላይ ያተኮረ የግምገማ መድረክ በደብረ ብርሃን ከተማ አካሂዷል።


የቢሮው ሃላፊ አቶ እንድሪስ አብዱ በመድረኩ ላይ እንዳሉት ኢንዱስትሪዎቹ ባለፉት ሰባት ወራት በኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ በመታገዝ የወጭ ንግድና ተኪ ምርት እያመረቱ ይገኛሉ።

ኢንዱስትሪዎቹ ከ258 ሺህ ቶን በላይ ምርቶች ማምረት መቻላቸውን ገልጸው ወደ ውጭ ከሚላኩ ምርቶችም የቢራና ለስላሳ ጠርሙስ፣ ጨርቃ ጨርቅ የሚገኙበት ሲሆን በተኪ ምርት ደግሞ የኮንስትራክሽንና ኢንዱስትሪ ግብአቶች ይገኙበታል።

በማያያዝም ባለፉት ሰባት ወራት በኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ዘርፍ ከ36 ሺህ በላይ ለሆኑ ዜጎች የስራ እድል መፈጠሩን አረጋገጠዋል።


የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ አቶ በድሉ ውብሸት እንዳሉት አምራች እንዱስትሪዎችን በመሳብ ሰፊ ጥረት እየተደረገ ነው ብለዋል።

የከተማ አስተዳደሩ የአምራች ኢንዱስትሪውን ዘርፍ ለማበረታት በማሰብ በዘርፉ የተሰማሩ ባለሃብቶች ብቻ የሚስተናገዱበት በሳምንት አንድ ቀን በመወሰን ጥያቄያቸው እንዲፈታ እየተደረገ ነው ብለዋል።

የደብረ ብርሃን ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት መምሪያ ሃላፊ አቶ ብርሃን ገብረህይወት በበኩላቸው በኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ከባለሀብቱ ጋር በየጊዜው በሚካሄድ ውይይት ችግሮች እየተፈቱ ነው ብለዋል።


የኢንዱስትሪ መንደሮችን መሰረት ልማት ለማሟላት በተደረገ ጥረትም ባለሀብቱን በማስተባበር የጠጠር መንገድና የኤሌትሪክ መስመር ዝርጋታ እየተከናወነ እንደሚገኝ አስረድተዋል።

ከተማዋን የኢንዱስትሪ፣ የቱሪዝምና የልቀት ማእከል ለማድረግ ታቅዶ እየተሰራ መሆኑን ገልጸው ለቀጣይ ኢንዱስትሪ ልማት የሚውል ከሁለት ሺህ ሄክታር መሬት መዘጋጀቱን ተናግረዋል።

የኮምበልቻ ከተማ አስተዳደር ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት መምሪያ ሃላፊ አቶ ሁሴን ሙሄ ይመር እንዳሉት ቅንጅታዊ አሰራርን በማጠናከር የኢንቨስትመንት ፍሰቱን ለማሳደግ እየተሰራ ነው ብለዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.