
ሀላባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ):- የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንገዶች ባለስልጣን በሀዲያና ሀላባ ዞኖች ከ61 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ ያስገነባቸው ሁለት የገጠር መንገድ ፕሮጀክቶች ተመርቀው ለአገልግሎት ክፍት ሆኑ።
መንገዶቹ በሀላባ ዞን ዌራ ዲጆ ወረዳ አሻሹሬ-ሚቶ እና በሀድያ ዞን ጌሜዶ-ሞርሲጦ 29 ኪሎ ሜትር የሚሸፍኑ ሁለት የገጠር መንገዶች ከ61 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ ተደርጎባቸዋል ተብሏል።

በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የክልሉ የመሰረተ ልማት ክላስተር አስተባባሪና የትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ ኃላፊ መሀመድ ኑርዬ (ዶ/ር) እንዳሉት፣ የመንገድ መሰረተ ልማት ተደራሽነት የክልሉን ፈጣን እድገት ለማረጋገጥ ያግዛል።
የገጠሩን ማህበረሰቡ የኢኮኖሚ ለማሳደግ የተጀመረውን ጥረት ከግብ ለማድረስ የመንገድ መሰረተ ልማት ተደራሽነት ማስፋት ቀዳሚ በመሆኑ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶት እየተሰራ ነው ብለዋል።
የክልሉ መንገዶች ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ምስጋና ማቲዎስ በበኩላቸው በክልሉ በርካታ የገጠር መንገዶችን በመገንባትና በመጠገን አገልግሎት እንዲሰጡ በማድረግ ላይ እንደሚገኝ ተናግረዋል።
በሁለቱ ዞኖች የተመረቁ 29 ኪሎ ሜትር የሚሸፍኑ የገጠር መንገዶች ከ61 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ መውጣቱን ጠቅሰዋል።
አስተያየታቸውን የሰጡት የአካባቢው ነዋሪዎችም በዕለቱ ተመርቆ አገልግሎት መስጠት የበቁ መንገዶች ዘርፈ ብዙ ችግሮችን እንደሚቀርፍላቸው ተናግረዋል።
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 11/2018 (ኢዜአ)፡- ቱሪዝም የኢኮኖሚያችን አንዱ ምሰሶ እንደመሆኑ የሀገራዊ ዕድገታችንን የወደፊት አቅጣጫ እየቀረጸ ያለ ዘርፍ መሆኑ...
Apr 20, 2026
ጅማ፤ ሚያዝያ 6/2018(ኢዜአ)፡- በጅማ የኮደርስ ስልጠና የወሰዱ የመንግሥት ሠራተኞች ቀልጣፋና ዘመናዊ የሕዝብ አገልግሎት መስጠት እንዲችሉ እያገዛቸው መሆኑን...
Apr 14, 2026
አምቦ፤ መጋቢት 17/2018 (ኢዜአ)፦ በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሸዋ ዞን የፍራፍሬ ልማትን የማስፋፋት ስራ በትኩረት እየተከናወነ መሆኑን የዞኑ አስተዳደር ገለጸ።...
Mar 27, 2026
በሙሴ መለሰ ኢትዮጵያ የዓለም የንግድ ድርጅት አባል ለመሆን ለመጀመሪያ ጊዜ ጥያቄ ያቀረበችው እ.አ.አ 2003 ነበር። ኢትዮጵያ በወቅቱ ጥያቄውን ካቀረበች በ...
Mar 27, 2026