የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ልዩ ዘገባ

<p>የመንግሥት የኤሌክትሮኒክ ግዥ በሁሉም የመንግስት ተቋማትና የንግዱ ማህበረሰብ ዘንድ ተመራጭ እየሆነ መጥቷል</p>

Mar 5, 2025

IDOPRESS

አዲስ አበባ፤ የካቲት 25/2017(ኢዜአ)፦ የመንግሥት የኤሌክትሮኒክ ግዥ በሁሉም የመንግስት ተቋማትና የንግዱ ማህበረሰብ ዘንድ ተመራጭ እየሆነ መምጣቱን የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ እዮብ ተካልኝ(ዶ/ር) ገለጹ።


በበጀት ዓመቱ ስድስት ወራት ከ303 ቢሊየን ብር በላይ የዋጋ ግምት ያላቸው 24 ሺህ የመንግስት የኤሌክትሮኒክ ግዥዎች እየተከናወኑ መሆኑን የመንግሥት ግዥና ንብረት ባለስልጣን አስታውቋል።


የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታው ለኢዜአ እንደገለጹት የመንግሥት የኤሌክትሮኒክ ግዥ በሁሉም የመንግስት ተቋማትና የንግዱ ማህበረሰብ ዘንድ ተመራጭ እየሆነ መጥቷል።


በተለይም መተግበሪያው የለማው በሀገር ውስጥ ባለሙያዎች መሆኑ ያሉበትን ውስንነቶች በየጊዜው እያሻሻሉ ለመሄድ እድል ፈጥሯል ብለዋል፡፡


የመንግሥት ግዥና ንብረት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር መስረት መስቀሌ፤ የመንግሥት ተቋማት የኤሌክትሮኒክ ግዥ ፍላጎት በየጊዜው እየጨመረ መምጣቱን ገልጸዋል፡፡


የግዥ ስርዓቱ በአዋጅ እንዲደገፍ በመደረጉ በንግዱ ማህበረሰብ እና የመንግስት ተቋማት መካከል ትስስር ፈጥሯል ብለዋል፡፡


የመንግሥት ተቋማት በኤሌክትሮኒክ ግዥ ስርዓት ለመጠቀም ያላቸው ቁርጠኝነትና ዝግጁነት የሚደነቅ ነው ያሉት ዋና ዳይሬክተሯ፤ ሁሉም የፌዴራል ተቋማት ግዥያቸውን በኤሌክትሮኒክ ግዥ ስርዓት ማቀዳቸውን ገልጸዋል፡፡


በዚህም በ2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያዎቹ ስድስት ወራት እስከ ታህሳስ 30 ቀን 2017 ዓ.ም ብቻ ከ303 ነጠብ 9 ቢሊየን ብር የዋጋ ግምት ያላቸው 24 ሺህ የመንግስት የኤሌክትሮኒክ ግዥዎች እየተከናወኑ መሆኑን ገልጸዋል፡፡


የዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂን ውጤታማ ለማድረግ ሁሉ ተቋማት ኃላፊነታቸውን መወጣት ይገባቸዋል ብለዋል።


የመንግስት የኤሌክትሮኒክ ግዥ ስርዓት በ2016 በጀት ዓመት ከነበረው መሻሻሉን የገለጹት ዋና ዳይሬክተሯ፤ የተሽከርካሪ አጠቃቀም እና ቁጥጥር በኢ- ፍሊት አስተዳደር ስርዓት የሙከራ ትግበራ እየተከናወነ መሆኑን ተናግረዋል፡፡


በቀጣይ በኢትዮጵያ ያሉ የመንገድ፣ ድልድይ፣ መስኖ፣ ሕንፃ እና ሌሎች ሀብቶችን በአንድ ማዕከል በዲጂታል መንገድ መዝግቦ የሚይዝ ስርዓት ለማልማት ዝግጅት እየተደረገ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡


#Ethiopian_News_Agency


#ኢዜአ #Ethiopia

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.