የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ልዩ ዘገባ

<p>ለምርት ዘመኑ ከ658 ሺህ ሜትሪክ ቶን በላይ የአፈር ማዳበሪያ ወደ ሀገር ውስጥ ተጓጉዟል</p>

Mar 5, 2025

IDOPRESS

አዲስ አበባ፤ የካቲት 25/2017(ኢዜአ)፡- ለ2017/18 የምርት ዘመን እስከ አሁን ከ658 ሺህ ሜትሪክ ቶን በላይ የአፈር ማዳበሪያ ወደ ሀገር ውስጥ መጓጓዙን የትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ ሚኒስቴር አስታወቀ።

ለምርት ዘመኑ ግብዓት የሚሆን 24 ሚሊዮን ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ ግዢ ለመፈጸም ታቅዶ እስከ የካቲት 23/2017 ዓ.ም. ድረስ 700 ሺህ 763 ሜትሪክ ቶን ማዳበሪያ ጅቡቲ ወደብ መድረሱን ሚኒስቴሩ ገልጿል።

ጅቡቲ ወደብ ከደረሰው የአፈር ማዳበሪያ መካከልም እስከተጠቀሰው ዕለት ድረስ 658 ሺህ 249 ሜትሪክ ቶን የአፈር ማዳበሪያ ወደ ሀገር ውስጥ መጓጓዙ ተመላክቷል።

የአፈር ማዳበሪያው በ13 መርከቦች ተጭኖ ጅቡቲ ወደብ ደርሷል።

ወደ ሀገር ውስጥ ከተጓጓዘው ውጭ 42 ሺህ 513 ነጥብ 9 ሜትሪክ ቶን የአፈር ማዳበሪያ በወደብ ላይ እንደሚገኝም ተገልጿል።

ወደ አገር ውስጥ ከተጓጓዘው ውስጥ 418 ሺህ 670.2 ሜትሪክ ቶን ዳፕ እንዲሁም 239 ሺህ 579 ሜትሪክ ቶን ደግሞ ዩሪያ የተሰኘው የአፈር ማዳበሪያ አይነት ነው።

ማዳበሪያው በባቡር እና በድንበር ተሻጋሪ የደረቅ ጭነት ተሽከርካሪዎች ወደ ሀገር ውስጥ መጓጓዙን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.