አዲስ አበባ ፤መጋቢት 4/2017(ኢዜአ)፦የንግድ እና ቀጠናዊ ሚንስትር ካሳሁን ጎፌ ( ዶ/ር) ሰብሳቢነት የቁም እንስሳት የወጪ ንግድን አስመልክቶ በበይነ-መረም ውይይት ተደርጓል።
በውይይቱም በዘርፉ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመፍታት በተለይም የኮንትሮባንድ ንግድ እንዲሁም የላኪዎችን አቅም ከማጠናከር አንፃር ያሉ ውስንነቶችን ለመቅረፍ መወሰድ ያለባቸው እርምጃዎች ዙሪያ ምክክር አድርገዋል።
በቀጣይም ኢትዮጵያ ካላት ከፍተኛ የቁም እንስሳት ሀብት አንፃር በዘርፉ ተወዳዳሪ እንድትሆን ሌሎች የፌደራል ተቋማትንም በማካተት ቀጣይነት ባለው መልኩ በቅንጅት ለመስራት ተስማምተዋል።
በውይይቱ ላይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የስራ ኃላፊዎች፣ የሚመለከታቸው የፌዴራል ተቋማት፣ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ኤምባሲ-ሪያድ እና የኢትዮጵያ ቆንሳላ ጄኔራል-ጂዳ እና በጂቡቲ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ኤምባሲ የሚሲዮን መሪዎች መሳተፋቸውን ጅቡቲ ከሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ የተገኝ መረጃ ያመለክታል።
#Ethiopian_News_Agency
#Ethiopia
#ኢዜአ