የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ልዩ ዘገባ

በባሌ ዞን ለዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያላቸው ችግኞች እየተዘጋጁ ነው

Mar 20, 2025

IDOPRESS

ሮቤ፤ መጋቢት 11/2017(ኢዜአ)፡- በኦሮሚያ ክልል ባሌ ዞን ለዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያላቸው ችግኞች እየተዘጋጁ መሆኑን የዞኑ ግብርና ጽህፈት ቤት ገለጸ።

በጽህፈት ቤቱ የተፈጥሮ ኃብት ልማት ባለሙያ አቶ ሙዘየን ሱልጣን ለኢዜአ እንዳሉት ችግኞቹ እየተዘጋጁ ያሉት በዞኑ 10 ወረዳዎች ነው።


እየተዘጋጁ ያሉት ችግኞች ለደን አገልግሎት የሚውሉና የፍራፍሬ ችግኝ ሲሆንበተለይ የአቮካዶ፣ የፓፓያ፣ ማንጎ፣ አፕል፣ ሙዝና ሌሎች የፍራፍሬ አይነቶች ትኩረት ማግኘታቸውን ተናግረዋል።

ዘንድሮ በመጠንም ሆነ በዓይነት ካለፈው ዓመት 20 በመቶ ብልጫ ያለው ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያለው ችግኝ እየተዘጋጀ መሆኑን አመልክተዋል።


የችግኝ ዝግጅቱን ውጤታማ ለማድረግ ከ213ሺህ ለሚበልጡ አርሶ አደሮችና በየደረጃው ለሚገኙ የግብርና ባለሙያዎች በችግኝ ዝግጅትና በተከላው ሂደት ላይ ያተኮረ የአቅም ግንባታ ሥልጠናና ሙያዊ ድጋፍ እየተደረገ መሆኑን አስረድተዋል።

ችግኝ የሚተከሉልበት ከ48 ሺህ ሄክታር በላይ የሚሆነውን መሬት የመለየት ስራ አስቀድሞ መከናወኑንም ጠቅሰዋል።

በዞኑ የሲናና ወረዳ ምክትል አስተዳዳሪና የግብርናና መሬት ልማት ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሙአዊያ ፉኣድ፤ በወረዳው በበጋው ወራት የአፈርና ውሃ እቀባ ስራ የተሰራባቸው አካባቢዎች ለአረንጓዴ አሻራ ሥራ ትልቅ እገዛ እንደሚያደርጉ ተናግረዋል።

የዘንድሮው የችግኝ ዝግጅት የአርሶ አደሩን የገቢ የሚያጎለብቱና የምግብ ዋስትናውን በማረጋገጥ ረገድ የተሻለ ጠቀሜታ ያለው ችግኝ ላይ አተኩሮ ዝግጅቱ እየተካሄደ ነው ብለዋል።

በአሁኑ ወቅትም ለወረዳው አርሶ አደሮችና በየደረጃው ለሚገኙ የግብርና ባለሙያዎች የችግኝመትከያ ጉድጓድ ዝግጅትን ጨምሮ በሌሎች ጉዳዮች በተግባር የተደገፈ የአቅም ግንባታ ሥልጠናና ሙያዊ ድጋፍ እየተደረገላቸው መሆኑን አመልክተዋል።

በተመሳሳይ በምእራብ ሸዋ ዞን ለመጪው ክረምት በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር የሚተከል ችግኝ እየተዘጋጁ መሆኑን የዞኑ ግብርና ጽህፈት ቤት አስታውቋል።


በጽህፈት ቤቱ የተፈጥሮ ሀብት ባለሙያ አቶ ጉደታ ጡሪ፤ በዞኑ የደን ሽፋንን ለማሳደግ የሚያግዝ እንዲሁም ለምግበነት የሚውሉ ፍራፍሬ በስፋት እየተዘጋጀ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ችግኙ እየተዘጋጀ ያለው በ5 ሺህ የመንግስት፣ የማህበራትና የግል ችግኝ ማፊያ ጣቢያዎች ውስጥ ሲሆን ስራው ተጠናከሮ መቀጠሉን ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.