
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 11/2017(ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ በአፍሪካ አንደኛ ስንዴ አምራች ሀገር መሆኗን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ገለጹ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት በኢኮኖሚው ዘርፍ ለተነሱላቸው ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ እየሰጡ ነው።
በማብራሪያቸውም መንግሥት የ10 ዓመት የልማት ዕቅድ ማዘጋጀቱን ገልጸው፤ ይህን እቅድ ከግብ ለማድረስ በትጋት እየሰራ ነው ብለዋል።
ኢትዮጵያ በዚህ ዓመት 8 ነጥብ 4 በመቶ የኢኮኖሚ ዕድገት ለማስመዝገብ አቅዳ እየሰራች መሆኗን ጠቅሰው፤ ባለፉት ስምንት ወራት በእያንዳንዱ ዘርፍ የተመዘገቡ አመላካች ውጤቶች ከታቀደው በላይ ማሳካት እንደሚቻል የሚያሳዩ ናቸው ሲሉ ገልጸዋል።
በግብርናው ዘርፍ አነስተኛ ይዞታ ያላቸው አርሶ አደሮች የሰብል ሽፋን አምና ከነበረበት 17 ነጥብ 5 ሚሊዮን ሄክታር ወደ 20 ነጥብ 5 ሚሊዮን ሄክታር ማደጉን ገልጸዋል።
በኩታ ገጠም እርሻ አምና የታረሰው 8 ነጥብ 7 ሚሊዮን እንደነበር ጠቅሰው፤ ዘንድሮ 11 ነጥብ 8 ሚሊዮን ሄክታር መታረሱን ተናግረዋል።
በስንዴ ልማት በመኸር 4 ነጥብ 2 ሚሊዮን ሄክታር፣ በበጋ መስኖ 3 ነጥብ 5 ሚሊዮን ሄክታር መልማቱን ጠቅሰዋል።
በዚህም 7 ነጥብ 7 ሚሊዮን ሄክታር መሬት በስንዴ ሰብል የሸፈነች ሲሆን ከዚህም ከ300 ሚሊዮን ኩንታል ያላነሰ ምርት ይጠበቃል ብለዋል።
በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያ በአፍሪካ ከፍተኛ ስንዴ አምራች ሀገር መሆኗንም አክለዋል።
ስንዴ ከውጭ ማስግባት የለባትም የሚል አቋም ለነበራቸው ሁሉ ከፍተኛ እመርታ መሆኑን ገልጸው፤ ይህ የማይካድ ሀቅ ነው ብለዋል።
በቡና፣ በአትክልትና ፍራፍሬ በቅባት እህሎች ባለፉት ዓመታት ከፍተኛ እመርታ መመዝገቡን ተናግረዋል።
በቡናው ዘርፍም ለውጭ ከቀረበ ምርት ባለፈው ዓመት 1 ነጥብ 4 ቢሊዮን ዶላር ገቢ መገኘቱን ጠቅሰው፤ ባለፉት ስምንት ወራት ብቻ 1 ነጥብ 2 ቢሊዮን ዶላር መገኘቱን ገልጸዋል።
በሚቀጥሉት አራት ወራትም አሁን ባለን አካሄድ ከፈጸምን 2 ቢሊዮን ዶላር አጠቃላይ ገቢ ማስመዝገብ እንችላለን ነው ያሉት።
ወልቂጤ ፤ሐምሌ 15/2018 (ኢዜአ)፦ በጉራጌ ዞን የመኸር አዝመራን ውጤታማ ለማድረግ ለሰብል እንክብካቤ፣ ለኩታገጠም እርሻና ለግብርና ቴክኖሎጂ አጠቃቀም ትኩ...
Jul 23, 2026
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 14/2018(ኢዜአ)፦ የተፈጥሮ ሀብትና የዱር እንስሳት ጥበቃ ሥራዎች ለቱሪዝም ዘርፍ ዕድገት ያላቸውን አስተዋጽኦ ይበልጥ የሚያጎሉ ተግባራት...
Jul 22, 2026
ድሬደዋ፣ሐምሌ 13/2018 (ኢዜአ)፦በድሬደዋ አስተዳደር በበጀት አመቱ ከ71 ቢሊዮን ብር በላይ ያስመዘገቡ ባለሃብቶች የኢንቨስትመንት ፈቃድ መውሰዳቸውን የአስተ...
Jul 21, 2026
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 7/2018 (ኢዜአ)፦ መንግሥት የኢትዮጵያን የሎጂስቲክስ ዘርፍ በማዘመን የገቢና የወጪ ንግድን ቀልጣፋ በማድረግ የኢንቨስትመንት ፍሰትን ለማ...
Jul 15, 2026