አዲስ አበባ፤ መጋቢት 23/2017(ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት አዲሱ የዲጂታልና ኢመርጂንግ ቴክኖሎጂ ኢኒሼቲቭ የነቃ ተሳትፎ እንደምታደርግ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ(ዶ/ር) ገለጹ።
ሚኒስትሩ ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ረዳት ዋና ፀሐፊ እና የዲጂታልና ኢመርጂንግ ቴክኖሎጂ ልዩ መልዕክተኛ አማንዲፕ ሲንግ ጊል(ዶ /ር) ጋር ዛሬ በጽህፈት ቤታቸው ተወያይተዋል።
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ረዳት ዋና ፀሐፊ እና የዲጂታልና ኢመርጂንግ ቴክኖሎጂ ልዩ መልዕክተኛ አማንዲፕ ሲንግ ጊል(ዶ /ር) ተመድ በዲጂታላይዜሽን እና በሰው ሰራሽ አስተውሎት ዙሪያ ባቋቋመው አዲስ ኢኒሼቲቭ ኢትዮጵያ አንድ አካል ሆና በንቃት እንድትሳተፍ ጥሪ አቅርበዋል።
ሚኒስትሩ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) የዲጂታላይዜሽን አስፈላጊነት ለሀገር እድገት ሊጫወት የሚችለውን ቁልፍ ሚና ከግምት ውስጥ በማስገባት በቴክኖሎጂ ዙሪያ የሚሰሩ የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት እና መሰል ተቋማት አስቀድሞ እንዲቋቋሙ ማድረጋቸውን ገልጸዋል።
ኢትዮጵያ የተመድ አዲሱ ኢኒሼቲቭ አካል መሆኗ ቁልፍ ተግባር እንደሆነ በመግለጽ በንቃት እንደምትሳተፍ አመልክተዋል።
አዲሱ የተመድ የዲጂታልና ኢመርጂንግ ቴክኖሎጂ ኢኒሼቲቭ በሰው ሰራሽ አስተውሎት ዙሪያ ወጥ የሆነ አስተዳደር ለማውጣትና የአቅም ግንባት ሥራዎችን ለመሥራት መቋቋሙን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
Jul 17, 2025
Apr 24, 2025
አዲስ አበባ፤የካቲት 4/2017(ኢዜአ)፦ የሲሚንቶ ንግድ እና መሰረታዊ የፍጆታ እቃዎችን በተመለከተ የወጡ መመሪያዎች ገበያውን በማረጋጋትና የዋጋ ግሽበትን በመቀ...
Feb 12, 2025