የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ልዩ ዘገባ

አዲስ አበባ ከተማን የኢንዱስትሪ ማዕከል ለማድረግ ዘርፈ ብዙ ስራዎች እየተከናወኑ ነው- ከንቲባ አዳነች አቤቤ

Apr 8, 2025

IDOPRESS

አዲስ አበባ፤መጋቢት 29/2017(ኢዜአ)፦ አዲስ አበባ ከተማን የኢንዱስትሪ ማዕከል ለማድረግ ዘርፈ ብዙ ስራዎች እየተከናወኑ እንደሚገኝ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ።

ከንቲባ አዳነች ከመንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር በመሆን ከተማ አቀፍ የኢትዮጵያ-አዲስ አበባ ታምርት የ2017 ዓ.ም የአምራች ኢንዱስትሪዎች አውደ ርዕይ ዛሬ በአዲስ ዓለም አቀፍ የኮንቬንሽን ማዕከል አስጀምረዋል።

ከንቲባዋ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፥የአምራች ኢንዱስትሪው ዘርፍ ቀዳሚ ትኩረት ከተሰጣቸው የኢኮኖሚ መስኮች መካከል አንዱ መሆኑን ገልጸዋል።

አዲስ አበባ ከተማን የኢንዱስትሪ ማዕከል ለማድረግ እየተከናወኑ ያሉ ስራዎችን በዝርዝር አስቀምጠዋል።

ፈጠራን ማበረታት፣ አምራቾችን መደገፍ፣ የፋይናንስ አቅርቦት፣ የመስሪያ ቦታዎችን ማመቻቸት፣ መሠረተ ልማትን ማሟላት፣ አስፈላጊ ሙያዊ ስልጠናዎችን መስጠት እንዲሁም ለአምራቾች ድጋፍ መስጠት እየተከናወኑ ካሉ ስራዎች መካከል ተጠቃሽ ናቸው።

እንደ ከንቲባዋ ገለጻ፤ የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ዘርፉን ከማነቃቃት ባለፈ በተለያዩ ምክንያቶች ማምርት አቁመው የነበሩ ኢንዱስትሪዎች ወደ ምርት ስራቸው እንዲመለሱ አድርጓል።

አምራቾች ምርታቸውን ለሸማቹ እንዲያስተዋውቁ፣ የገበያ ትስስር እንዲፈጥሩ፣ ሽያጭ እንዲያከናውኑ እና አምራቾች ከፍ ባለ መድረክ ተገኝተው ልምድ እንዲለዋወጡ የሚያደርግ መድረክ እንደሆነም አመልክተዋል።

የከተማዋ ነዋሪዎች ከ250 በላይ አምራች ኢንዱስትሪዎች የተሳተፉበትን አውደ ርዕይ እንዲጎበኙ ጥሪ አቅርበዋል።

በሀገር ምርት በመጠቀም፣የሀገር ውስጥ አምራቾችን በመደገፍ እና የሀገር ውስጥ ምርት በመግዛት አምራች እንዱስትሪዎችን ማበረታት እንደሚገባም ነው ከንቲባዋ በመልዕክታቸው ያሳሰቡት።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.