ጀሙ፤ መጋቢት 29/2017(ኢዜአ)፦ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ምዕራብ ኦሞ ዞን ይርኒ ቀበሌ ከ5ሺህ በላይ ዜጎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ የጸሐይ ኃይል ማመንጫ ተመርቆ አገልግሎት መስጠት ጀምሯል።
ፕሮጀክቱ በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር እና በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በቅንጅት በ60 ሚሊዮን ብር የተገነባ ነው።
የተመረቀው ፕሮጀክት 100 ኪሎ ዋት ኃይል ማመንጨት የሚችል መሆኑን የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ዴኤታ ኢንጂነር ሱልጣን ወሊ(ዶ/ር) ተናግረዋል።
ኢኮኖሚያዊ ብልጽግናን ለማረጋገጥ መሰል ፕሮጀክቶች ትልቅ ትርጉም ስላላቸው ትኩረት ተሰጥቶ እየተሠራ መሆኑን ገልጸዋል።
በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ ላይ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴርና የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት እንዲሁም የክልሉና የዞን የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።