
ሆሳዕና፤ መጋቢት 29/2017 (ኢዜአ)፡- በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የማኑፋክቸሪንግ ዘርፉን በማጠናከር የዜጎችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በትኩረት እንደሚሰራ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) ገለጹ።
የማኑፋክቸሪንግ ዘርፉን ማጠናከር ላይ ያለመ የምክክር መድረክ ዛሬ በሆሳዕና ከተማ ተካሄዷል፡፡

ርዕሰ መስተዳድሩ በዚህ ወቅት እንዳሉት ክልሉ የሀገር ውስጥና የውጪ ባለሀብቶችን በዘርፉ ኢንቨስት እንዲያደርጉ የሚያስችሉ አማራጮችን ተግባራዊ በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡
አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞችን በማስፋትና በመደገፍ ለስኬት እንዲበቁ ማስቻል ለስራ እድል ፈጠራ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክትም ተናግረዋል፡፡
በአገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያ ያሉ ተግዳሮቶችን መፍታት፣ የማምረቻና የመሸጫ ቦታዎች ማዘጋጀትን ጨምሮ በማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ የሚስተዋሉ ማነቆዎችን ለመፍታት ትኩረት ተሰጥቶ እንደሚሰራ ተናግረዋል።
በክልሉ የማኑፋክቸሪንግ ዘርፉን በማጠናከር የዜጎችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እንደሚሰራም ገልፀዋል፡፡
በወተት፣ በንብ ማነብና በሌሎች ዘርፎች የተሰማሩ አደረጃጀቶችን በመጠቀም የሚያመርቱትን ምርት እሴት በመጨመር ምርታቸውን ለገበያ እንዲያቀርቡ ማድረግ እንደሚገባም ጠቁመዋል።

የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ዋና ዳይሬክተር አለባቸው ንጉሴ (ዶ/ር) በበኩላቸው በኢንተርፕራይዝ ዘርፍ የሚስተዋሉ ችግሮችንና የመፍትሄ አቅጣጫዎችን የሚያመላክት እንዲሁም የድጋፍ ማዕቀፍን መሰረት ያደረገ ጥናት በመከናወን ላይ መሆኑን ተናግረዋል።
በማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ የሚስተዋሉ ችግሮችን በዘላቂነት በመፍታት ከባለድርሻ አካላት ጋር ተጨባጭ ውጤት ለማምጣት እንደሚሰራም ነው ያስረዱት፡፡

የክልሉ ስራ እድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዞች ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሙስጠፋ ኢሳ እንደገለፁት በክልሉ ተወዳዳሪና አምራች ኢንተርፕራይዞችን በማፍራት የዜጎችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እየተሰራ ነው።
በዚህም ለ1 ሺህ 286 አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ሁሉን አቀፍ ድጋፍ በመስጠት ወደ ኢንዱስትሪ ለማሳደግ ጥረት እየተደረገ እንደሚገኝም ጠቁመዋል።
በመርሐ ግብሩ ላይ የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት የክልል፣ የዞንና፣ የልዩ ወረዳ ከፍተኛ አመራሮችን ጨምሮ በተለያየ ዘርፍ የተሰማሩ ባለሀብቶች ተሳትፈዋል፡፡
ባሕርዳር፤ ጳግሜ 5/ 2018 (ኢዜአ) ፡-የሀገርን ቀጣይ ተስፋ እና የትውልዱን እጣ ፋንታ የተሻለ ለማድረግ የዛሬው ብርታትና ትጋታችን ወሳኝ ነው ሲሉ የአማራ ...
Sep 11, 2026
ወላይታ ሶዶ፤ ጳጉሜን 4/2018 (ኢዜአ) ፦በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ለዘመን መለወጫ በዓል የምርት አቅርቦት እጥረት እንዳይከሰት በቂ ዝግጅት መደረጉን የክልሉ ን...
Sep 10, 2026
ባህር ዳር፤ ጳጉሜን 1/2018 (ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የግብርናውን ዘርፍ ከአምራች ኢንዱስትሪው ጋር በማስተሳሰር ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ መቻሉን የክልሉ ...
Sep 7, 2026
ጋምቤላ፤ ነሐሴ 24/2018 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ለአሳ አጥማጆች የተደረገው የግብአት ድጋፍ አበረታች ውጤት እያስገኘ መሆኑን የክልሉ እንስሳትና ዓሳ ሃ...
Aug 31, 2026