የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ልዩ ዘገባ

በክልሉ በመጪው የበዓል ወቅት በፍጆታ ምርት ላይ ያልተገባ የዋጋ ጭማሪ እንዳይከሰት ዝግጅት እየተደረገ ነው

Apr 9, 2025

IDOPRESS

ባህርዳር፤መጋቢት 30/2017(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል በመጪው የፋሲካ በዓል ወቅት በፍጆታ ምርት ላይ ያልተገባ የዋጋ ጭማሪ እንዳይከሰት ከወዲሁ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የክልሉ ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ አስታወቀ።


ከዝግጅቱም መካከል ጊዜያዊ የገበያ ማዕከላት፣የንግድ ትርኢትና ባዛሮች እንደሚገኙበት ተመልክቷል።


የክልሉ ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ኃላፊ ኢብራሂም ሙሃመድ(ዶ/ር) ማምሻውን በሰጡት መግለጫ፤ በቅርቡ በሚከበረው የፋሲካ በዓል የአቅርቦት እጥረት እንዳይፈጠር እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።


በዚህም ቀደም ሲል በሌማት ትሩፋት ላይ በተከናወነው ስራ እንቁላል፣ ዶሮና ሌሎች የግብርና ምርቶችን ከደላላ ነጻ በሆነ የግብይት አሰራር ለማቅረብ የሚያስችል ዝግጅት መደረጉን ጠቅሰዋል።


በተጨማሪም የደለቡ ሠንጋ በሬዎች፣ በግ፣ ፍየልና ሌሎች ለበዓሉ የሚውሉ ግብአቶች ከተለያዩ የገጠር አካባቢዎች እንዲገቡ ቀድሞ የማመቻቸት ስራ መከናወኑን አስረድተዋል።


እንደ ዘይት፣ስኳርና ዱቄት ያሉ የኢንዱስትሪ ምርቶች በበቂ ሁኔታ እየቀረቡ በመሆኑ ሸማቹ ህብረተሰብ ተረጋግቶ እንዲገበያይ አስታውቀዋል።


የተሳለጠ ግብይት እንዲኖርና ታልተገባ የዋጋ ጭማሪ እንዳይከሰት በክልሉ ሁሉም አካባቢዎች ጊዜያዊ የገበያ ማዕከላት መዘጋጀታቸውን ጠቁመው፤ የንግድ ትርኢትና ባዛር ለማሰናዳት በሂደት ላይ እንዲሆኑ አረጋግጠዋል።


በየደረጃው የሚገኙ የቢሮው መዋቅር አመራር አባላትና ባለሙያዎች የተሳለጠ ግብይት እንዲኖር አስፈላጊውን ክትትልና ድጋፍ ማድረግ እንዳለባቸው አሳስበዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.