
አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 1/2017(ኢዜአ)፦ መንግስት ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን ለሚተኩ አምራች ኢንዱስትሪዎች እድገት ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን የኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበል ገለጹ።
አቶ መላኩ አለበል ሳቢያን ቤዝ ሜታል ኢንጂነሪንግ የተባለ ተቋምን የስራ እንቅስቃሴ ጎብኝተዋል።
ሚኒስትሩ በጉብኝቱ ወቅት መንግስት ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን በሀገር ውስጥ ምርት ለሚተኩ አምራች ኢንዱስትሪዎች መስፋፋት ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል።
በዚህም መንግስት የተለያዩ ድጋፎችን በማድረግ ፋብሪካዎች እንዲስፋፉ እያደረገ ይገኛል ብለዋል፡፡
ዛሬ የተጎበኘው ሳቢያን ቤዝ ሜታል ኢንጂነሪንግ ከውጭ የሚገባውን የውሀ ቆጣሪ በሀገር ውስጥ ምርት በመተካት ረገድ ትልቅ አስተዋጽኦ እያበረከተ ይገኛል ብለዋል፡፡
መንግስት ይበለጠ ተኪ ምርትን የሚያመርቱ ፉብራካዎች እንዲስፋፉ እና ውጤታማ እንዲሆኑ ድጋፉና ክትትሉን አጠናክሮ እንደሚቀጥልም አስታውቀዋል።
የሳቢያን ቤዝ ሜታል ኢንጂነሪንግ ስራ እስኪያጅ ዐይንእሸት አስረስ(ዶ/ር) መንግስት በሚያደርግላቸው ድጋፍ ድርጅቱ ውጤታማ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ባሕርዳር፤ ጳግሜ 5/ 2018 (ኢዜአ) ፡-የሀገርን ቀጣይ ተስፋ እና የትውልዱን እጣ ፋንታ የተሻለ ለማድረግ የዛሬው ብርታትና ትጋታችን ወሳኝ ነው ሲሉ የአማራ ...
Sep 11, 2026
ወላይታ ሶዶ፤ ጳጉሜን 4/2018 (ኢዜአ) ፦በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ለዘመን መለወጫ በዓል የምርት አቅርቦት እጥረት እንዳይከሰት በቂ ዝግጅት መደረጉን የክልሉ ን...
Sep 10, 2026
ባህር ዳር፤ ጳጉሜን 1/2018 (ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የግብርናውን ዘርፍ ከአምራች ኢንዱስትሪው ጋር በማስተሳሰር ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ መቻሉን የክልሉ ...
Sep 7, 2026
ጋምቤላ፤ ነሐሴ 24/2018 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ለአሳ አጥማጆች የተደረገው የግብአት ድጋፍ አበረታች ውጤት እያስገኘ መሆኑን የክልሉ እንስሳትና ዓሳ ሃ...
Aug 31, 2026