የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ

የግብርናውን ዘርፍ ማዘመንና ምርታማነትን ማሳደግ የሚያስችል ዘመናዊ አሰራርን መከተል ይገባል

Apr 15, 2025

IDOPRESS

መቀሌ፤ ሚያዚያ 6/2017(ኢዜአ)፦ የግብርናውን ዘርፍ ማዘመንና ምርታማነትን ማሳደግ የሚያስችል ዘመናዊ አሰራርን መከተል ይገባል ሲሉ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ሌተናል ጀነራል ታደሰ ወረደ ገለጹ።

የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር የእርሻና ተፈጥሮ ሃብት ቢሮ ከባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር ያዘጋጀው የግብርና ስትራቴጂክ ትግበራ እቅድን በተመለከተ በመቀሌ ከተማ ውይይት ተካሂዷል።

በመድረኩ ላይ ንግግር ያደረጉት የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ሌተናል ጀነራል ታደሰ ወረደ፤ የግብርናውን ዘርፍ ማዘመንና ምርታማነትን ማሳደግ የሚያስችል ስትሬቴጅክ አሰራርን መከተል ይገባል ብለዋል።


የግብርና ልማትን ውጤታማ ለማድረግ በነበረው ስትራቴጂ እና ፖሊሲ መቀጠል የማይቻል በመሆኑ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን በማከል ውጤታማ ለመሆን መስራት ይገባል ብለዋል።

በመሆኑም በክልሉ የተፈጥሮ ሃብትን በመጠበቅ ዘመናዊ አሰራሮችን በመከተልና የተቀናጁ ጥረቶችን በማድረግ ማልማት አስፈላጊ መሆኑን አንስተዋል።

በዚሁ ዙሪያ የተዘጋጀውን የስትራቴጂክ አተገባበር ውጤታማ ለማድረግና በተለይም የገጠሩን ማህበረሰብ አኗኗር ለማሻሻል በቅንጅት መስራት ተገቢ መሆኑን ጠቅሰው በዚህ ረገድ የክልሉ መንግስት አስፈላጊውን ድጋፍና እገዛ የሚያደርግ መሆኑን አረጋግጠዋል።


በጊዜያዊ አስተዳደሩ የእርሻና ተፈጥሮ ሀብት ቢሮ ሀላፊ እያሱ አብረሃ(ዶ/ር) የስትራቴጂው ትኩረት ግብርናን ማዘመንና ምርታማነትን ማሳደግ መሆኑን ገልጸዋል።

የግብርና ዘርፉን ማዘመንና ምርታማነትን ማሳደግ ከተቻለ ከተረጅነት በመውጣት በተለይም የገጠሩን ማህበረሰብ አኗኗር ማሻሻል የሚያስችል ይሆናልም ነው ያሉት።

አጠቃላይ ስትራቴጅክ እቅዱ የመሬትና ውሃ አስተዳደር፣ እንስሳት እና የተፈጥሮ ሃብት ልማትን፣ የእርሻ ግብአት አጠቃቀምና ማዘመን እንዲሁም የገጠር ፋይናንስ አቅርቦትን ማእከል ያደረገ ስለመሆኑም አስረድተዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.