አዲስ አበባ ፤ ሚያዚያ 14/2017 (ኢዜአ)፡- ዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (አይኤምኤፍ) ለኢትዮጵያ እድገት እና ልማት የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል የድርጅቱ ማኔጂንግ ዳይሬክተር ክርስታሊና ጆርጂዬቫ ገለጹ።
የዓለም ባንክ ግሩፕ እና የዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (አይኤምኤፍ) ዓመታዊ የፀደይ ወቅት ስብሰባ ትናንት በዋሺንግተን ዲሲ ተጀምሯል።
የዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (አይኤምኤፍ) ማኔጂንግ ዳይሬክተር ክሪስታሊና ጂኦርጂዬቫ ከስብስባው ጎን ለጎን ከገንዘብ ሚኒስትር አቶ አሕመድ ሽዴ እና ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ አቶ ማሞ ምህረቱ ጋር ተወያይተዋል።
ማኔጂንግ ዳይሬክተሯ የኢትዮጵያን ሪፎርም አጀንዳ አስመልክቶ ውይይት ማድረጋቸውን በኤክስ ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ገልጸዋል።
አይኤምኤፍ የኢትዮጵያን እድገት እና ልማት ለመደገፍ ቁርጠኛ መሆኑንም አመልክተዋል።
የዓለም ባንክ ግሩፕ እና የዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (አይኤምኤፍ) ዓመታዊ የፀደይ ወቅት ስብሰባ እስከ ሚያዚያ 18 ቀን 2017 ዓ.ም ይቆያል።