የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ

የጥራት መንደሩ የኢትዮጵያ ምርት በአለም አቀፍ ደረጃ ተቀባይነቱ እንዲጨምር በማድረግ በኩል ትልቅ አስተዋጽኦ አለው -ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶር)

Apr 27, 2025

IDOPRESS

አዲስ አበባ፤ሚያዝያ 18/2017(ኢዜአ)፦የጥራት መንደሩ መገንባት የኢትዮጵያ ምርት በአለም አቀፍ ደረጃ ተቀባይነቱ እንዲጨምር በማድረግ በኩል ትልቅ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) ገለፁ።


የኢትዮጵያ ተስማሚነት ምዘና ድርጅት የጥራት መንደር መገንባት የተቀናጀና ደረጃውን የጠበቀ እንዲሁም ጥራት ያለው አገልግሎት መስጠት ማስቻሉንም ተጠቅሷል።


ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ንግድ ተወዳዳሪ መሆን የሚያስችላትን የጥራት መንደር ባለፈው ህዳር ወር 2017 ዓ.ም መርቀው ለአገልግሎት ክፍት ማድረጋቸው ይታወሳል።


የጥራት መንደር የኢትዮጵያ ደረጃዎች ኢንስቲትዩት፣ የኢትዮጵያ ተስማሚነት ምዘና ድርጅት፣ የኢትዮጵያ ስነ ልክ ኢንስቲትዩት፣ የኢትዮጵያ አክሪዲቴሽን አገልግሎት እና የኢትዮጵያ ቴክኖሎጂ ባለስልጣንን የያዘ ነው፡፡


የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) ቀደም ብሎ ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ እንዳሉት፤ የጥራት መንደሩ በበርካታ የአፍሪካ ሀገራት በብዛት የማይገኙ የሴራሚክ፣ የባትሪ እና የሶላር ሀይል ማመንጫ መሳሪያዎችን መፈተሽ የሚያስችሉ ላቦራቶሪዎችን ጭምር ያካተተ ነው፡፡


በዚህም ኢትዮጵያ በአፍሪካ ግዙፉን የጥራት መንደር መገንባቷን ነው ያነሱት፡፡


የጥራት መንደሩ በመገንባቱ ደረጃቸውን የጠበቁ የአሰራር ስርዓቶች በመዘርጋት በአለም አቀፍ ደረጃ የነበረንን ተቀባይነት እንዲጨምር የሚያስችል እንደሆነም ነው የገለፁት።


የኢትዮጵያ ተስማሚነት ምዘና ድርጅት የማርኬቲንግ እና ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ተክኤ ብርሀነ በበኩላቸው፥ ድርጅቱ በዋናነት የጥራት ፍተሻ ላቦራቶሪ፣ የጥራት ሰርተፊኬሽን እና የኢንስፔክሽን አገልግሎቶችን እየሰጠ ይገኛል ብለዋል።


የጥራት መንደሩ መገንባት ኢትዮጵያ በምርት ጥራት ፍተሻ የነበራትን ተቀባይነት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ እንዲመጣ ማስቻሉንም ነው የተናገሩት።


በዚህም በውጭ ሀገራት የጥራት ፍተሻ ይደረግላቸው የነበሩ ምርቶችን በሀገር ውስጥ መፈተሽ የሚያስችል አቅም ፈጥሯል ነው ያሉት።


በሌላ በኩል አራቱ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት አንድ ላይ የያዘ በመሆኑ የተቀናጀና ደረጃውን የጠበቀ እንዲሁም ጥራት ያለው አገልግሎት ለመስጠት እንዳስቻለ አቶ ተክኤ ብርሃነ ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.