
ደሴ፤ሚያዚያ 24/2017 (ኢዜአ)፦የኮደርስ ስልጠና በዲጅታል ዘርፍ የኢትዮጵያን የምጣኔ ሃብት እድገት ለማሳለጥና ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪ ለማድረግ ፋይዳው የላቀ መሆኑን በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የክልሉ ከተሞች ልማት ክላስተር አስተባባሪና የከተማና መሰረተ ልማት ቢሮ ኃላፊ አህመዲን መሀመድ (ዶ/ር) ገለጹ።
በአማራ ክልል በዘጠኝ ወራት የተከናወኑ የኮደርስ ስልጠና አፈጻጸም በተመለከተ በደሴ ከተማ የውይይት መድረክ ተካሂዷል።
አህመዲን መሀመድ (ዶ/ር) በመድረኩ ላይ እንደገለጹት፥ የኮደርስ ስልጠና በዲጅታል ዘርፍ የኢትዮጵያን የምጣኔ ሃብት እድገት ለማሳለጥና ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪ ለማድረግ ፋይዳው የላቀ ነው።
ለዚህም መንግስት ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን አንስተው፥ በተለይም ወጣቶች የኮደርስ ስልጠና እድል ተጠቃሚ ለመሆን መትጋት አለባቸው ብለዋል።
የኮደርስ ስልጠና በእውቀት እና ክህሎት ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪ የሚያደርግ በመሆኑ አጋጣሚው እንዳያመልጥ ሁሉም ሊሰለጥን እንደሚገባም አንስተዋል።
በመሆኑም በቀጣይ በተለይም ወጣቶች ስልጠናው ሊያመልጣቸው እንደማይገባ አንስተው፥በተለይ ዩኒቨርሲቲዎችና የቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች የስልጠና ክፍል በማዘጋጀትና ግብዓት በማሟላት ኃላፊነታቸውን ሊወጡ ይገባል ብለዋል።
የአማራ ክልል ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ የቻለ ይግዛው፥የኮደርስ ስልጠና በቴክኖሎጂ የዳበረ ትውልድ ለመፍጠር ከፍተኛ ሚና እንዳለው ተናግረዋል።
በዚህም በክልሉ ስልጠናውን በማጠናከር ቴክኖሎጂን፣ክህሎትንና ዘመናዊ አሰራሮችን ለማስፋፋትና ለማሻሻል በቅንጅት እየተሰራ መሆኑን አመልክተዋል።
በበጀት ዓመቱ ከ192 ሺህ ለሚበልጡ ዜጎች ስልጠናውን እንዲወስዱ ታቅዶ እስካሁን ከ100 ሺህ በላይ ዜጎች መሰልጠናቸውን ተናግረዋል።
በመድረኩ የክልል፣የዞንና የከተማ አስተዳደር አመራሮችን ጨምሮ ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል።
ባሕርዳር፤ ጳግሜ 5/ 2018 (ኢዜአ) ፡-የሀገርን ቀጣይ ተስፋ እና የትውልዱን እጣ ፋንታ የተሻለ ለማድረግ የዛሬው ብርታትና ትጋታችን ወሳኝ ነው ሲሉ የአማራ ...
Sep 11, 2026
ወላይታ ሶዶ፤ ጳጉሜን 4/2018 (ኢዜአ) ፦በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ለዘመን መለወጫ በዓል የምርት አቅርቦት እጥረት እንዳይከሰት በቂ ዝግጅት መደረጉን የክልሉ ን...
Sep 10, 2026
ባህር ዳር፤ ጳጉሜን 1/2018 (ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የግብርናውን ዘርፍ ከአምራች ኢንዱስትሪው ጋር በማስተሳሰር ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ መቻሉን የክልሉ ...
Sep 7, 2026
ጋምቤላ፤ ነሐሴ 24/2018 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ለአሳ አጥማጆች የተደረገው የግብአት ድጋፍ አበረታች ውጤት እያስገኘ መሆኑን የክልሉ እንስሳትና ዓሳ ሃ...
Aug 31, 2026