የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ

ግብርናን በተሻለ መንገድ የሚመሩ የጥናትና ምርምር፣ አዳዲስና በቴክኖሎጂ የታገዙ አሰራሮችን የሚያሳልጡ ተቋማት ግንባታ በዘርፉ ከፍ ያለ እመርታ ያመጣሉ - ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ

May 21, 2025

IDOPRESS

አዲስ አበባ፤ ግንቦት 12/2017(ኢዜአ)፦ ግብርናን በተሻለ መንገድ የሚመሩ የጥናትና ምርምር፣ አዳዲስና በቴክኖሎጂ የታገዙ አሰራሮችን የሚያሳልጡ ተቋማት ግንባታ በዘርፉ ከፍ ያለ እመርታ የሚያመጡ ናቸው ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሁለተኛው የብራዚል-አፍሪካ የምግብ ዋስትና፣ ረሃብን መዋጋት እና የገጠር ልማት ጉባኤ በብራዚሏ ዋና ከተማ ብራዚሊያ መካሄድ መጀመሩን ገልጸዋል።


‎መድረኩ የግብርና ምርትን እድገት፣ የገጠር ልማትንና የምግብ ዋስትናን ማሻሻል ላይ ትኩረት ያደረገ መሆኑንም አስታውቀዋል።

‎ግብርናን በተሻለ መንገድ የሚመሩ የጥናትና ምርምር፣ አዳዲስና በቴክኖሎጂ የታገዙ አሰራሮችን የሚያሳልጡ ተቋማት ግንባታ በዘርፉ ከፍ ያለ እመርታ የሚያመጡ መሆናቸውንም ጠቁመዋል።

‎ኢትዮጵያ በፖሊሲ የተደገፈ መሰረታዊ የለውጥ ስራዎችን በመተግበር የግብርናውን ዘርፍ ከፍ ባለ እመርታ ላይ ለማስገኘት የሰራችውንና እየሰራች ያለውን ተሞክሮ በጉባዔው ታቀርባለች የሌሎችንም ትጋራለች ብለዋል።

‎በመድረኩ የእውቀት ሽግግር እና የደቡብ-ደቡብ ትብብርን በመጠቀም የምግብ ስርዓታችንን ሊያጠናክሩ የሚችሉ የመስክ ምልከታዎችን፣ የልምድ ልውውጦችንና ስምምነቶችን እያከናወኑ መሆናቸውን ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.