የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ

በክልሉ የንጹህ መጠጥ ውሃ አቅርቦትን ለሕብረተሰቡ ተደራሽ የማድረጉ ተግባር በውጤታማነት ቀጥሏል

May 30, 2025

IDOPRESS

ሻሸመኔ፤ግንቦት 20/2017(ኢዜአ)፡-በኦሮሚያ ክልል ንጹህ የመጠጥ ውሃ ለሕብረተሰቡ ተደራሽ የማድረጉን ተግባር በውጤታማነት ተጠናክሮ መቀጠሉን የክልሉ ውኃና ኢነርጂ ቢሮ አስታወቀ።

የመገናኛ ብዙሃን ሀላፊዎች እና ባለሙያዎች የተሳተፉበት የንጹህ መጠጥ ውኃ አቅርቦት እንቅስቃሴ ጉብኝት በሻሸመኔ እና አርሲ ነጌሌ ከተሞች ተካሄዷል።

በዚሁ ወቅት የክልሉ ውኃና ኢነርጂ ቢሮ ኃላፊ ኢንጂነር ሚሊዮን በቀለ፣ በክልሉ የንጹህ መጠጥ ውኃ ተደራሽነትን ማሳደግ የሚያስችሉ የሪፎርም አሰራሮች መተግበራቸውን ተናግረዋል።

እየተተገበረ ባለው ሪፎርም በክልሉ በርካታ አካባቢዎች የንጹህ መጠጥ ውኃ አርቦት ለሕብረተበሱ ተደራሽ እየሆነ መምጣቱን ገልጸው፥በተለይ በተቋሙ ውስጥ ያለውን አሰራር ማሻሻል በመቻሉ በዘርፉ ሕብረተሰቡ ለረጅም ጊዜ ሲያነሳው የቆየው የመልካም አስተዳደር ችግር መቀነስ መቻሉን አስረድተዋል።

በክልሉም ከዚህ ቀደም ግንባታቸው ተጀምሮ ያልተጠናቀቁ የንጹህ መጠጥ ውኃ ፕሮጀክቶች ግንባታን ለማጠናቀቅ በትኩረት እየተሰራ መሆኑንም ተናግረዋል።

ግንባታቸው የተጠናቀቀ ፕሮጀክቶችም ዘላቂነት ያለው የተቀላጠፈ አገልግሎት መስጠት እንዲችሉ ቢሮው አስፈላጊውን ክትትል እያደረገ መሆኑንም ገልጸዋል።

እንድ ሀላፊዋ ገለጻ፤ አገልግሎት መስጠት የጀመሩ ፕሮጀክቶች የሕብረተሰቡን የንጹህ መጠጥ ውኃ ችግር መፍታት ያስቻሉ ናቸው።

የተሻለ ውጤት ከተገኘባቸው የክልሉ አካባቢዎች መካከል ምዕራብ አርሲ ዞን አንዱ መሆኑን ጠቅሰው፥በዞኑ በርካታ የንጹህ መጠጥ ውኃ ፕሮጀክቶች መገንባታቸውን አመልክተዋል።

በዞኑ የተገነቡት የንጹህ መጠጥ ውኃ ፕሮጀክቶች በሻሸመኔ፣ በአርሲ ነጌሌ እና በአጄ ከተሞች የነበረውን ችግር ማቃለል ማስቻላቸውን አብራርተዋል።

የሻሸመኔ ከተማ የመጥ ውኃ እና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ደምሴ ኞሬ፣በከተማው የንጹህ መጠጥ ውኃን ተደራሽ ለማድረግ በተከናወነው ስራ ውጤት መገኘቱን ጠቁመዋል።

በተለይም ከለውጡ በኋላ በመንግስት በጀትና ሕዝቡን በማስተባበር የውኃ ተቋማት ግንባታዎች በትኩረት ሲከናወኑ ነበር።

የከተማው ነዋሪ ከገንዘብ በሻገር አምስት የውኃ ጉድጓድ መቆፈር መቻሉንም አስታውሰዋል።

ከተቆፈሩ ጉርግዶችም በቀን ከ17 ሺህ ሜትር ኪዩብ በላይ ውኃ ለነዋሪው ተደራሽ እየተደረገ መሆኑን ጨምረው ገልጸዋል።

ከሳኒቴሽን ጋር በተያያዘም የመጠጥ ውኃ እና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅቱ 72 የሕዝብ መጸዳጃ ቤቶችን ማስገንባቱን አስረድተዋል።

በጉብኝቱ ውቅት የተገኙ ከሻሸመኔ ከተማ የተወጣጡ ነዋሪዎችም በከተማው ከዚህ ቀደም የነበረው የንጹህ መጠጥ ውኃ አቅርቦት ችግር እየተቃለለ መምጣቱን አብራርተዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.