የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ

በኢንቨስትመንት ዘርፍ ተግባራዊ እየተደረገ ያለው ሪፎርም ምቹ የኢንቨስትመንት ከባቢን እየፈጠረ ነው - ኮሚሽነር ዘለቀ ተመስገን (ዶ/ር)

Jun 3, 2025

IDOPRESS

አዲስ አበባ፤ ግንቦት 23/2017(ኢዜአ)፦መንግስት በኢንቨስትመንት ዘርፍ ተግባራዊ እያደረገ ያለው ሪፎርም ምቹ የኢንቨስትመንትና ቢዝነስ ከባቢ እየፈጠረ መሆኑን የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ዘለቀ ተመስገን (ዶ/ር) ገለፁ።

የኦሮሚያ ክልል የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴና አማራጮች ዙሪያ ፎረም ተካሂዷል።


በፎረሙ የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት ሽመልስ አብዲሳ፣ የኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበል፣ የኦሮሚያ ኢንቨስትመንት እና ኢንዱስትሪ ቢሮ ኃላፊ አሕመድ እድሪስ እና ባለሃብቶች ተገኝተዋል።

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ዘለቀ ተመስገን(ዶ/ር) በዚሁ ወቅት እንዳሉት እንደ ሀገር ኢንቨስትመንትን ለማበረታታት በርካታ የሪፎርም ተግባራት መከናወኑን ተናግረዋል።

የህግን ጨምሮ የፖሊሲ፣ የአሰራር እና ሌሎች አስፈላጊ ማሻሻያዎች መደረጋቸውን አንስተዋል።

ማሻሻያዎቹ ተገማች የሆነ የኢንቨስትመንት እና የቢዝነስ ከባቢን ለመጥፈር እያስቻሉ መሆናቸውንም ገልጸው፤ ባለሃብቶች በምቹ ሁኔታ ኢንቨስት እንዲያደርጉ የሚያስችል መሆኑንም አስታውቀዋል።

ባለሃብቶች ይህን እድል በመጠቀም ኢንቨስት እንዲያደርጉም ጥሪ አቅርበዋል፡፡


የኢንዱስትሪ ሚኒስትር ዴኤታ ታረቀኝ ቡሉልታ በበኩላቸው ከለውጡ ወዲህ እንደ ሀገር የተወሰዱ የኢንቨስትመንት ማሻሻያዎች የኢንዱስትሪ ዘርፉን በከፍተኛ መጠን ማነቃቃቱን አንስተዋል።

በተለይ የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ አምራች ኢንዱስትሪውን ምርታማ እንዲሆን፣ የዘርፉ ማነቆዎች እንዲፈቱ እና ለተጨማሪ ኢንቨስትመንቶች ምቹ ሁኔታ መፍጠሩንም አስታውቀዋል፡

ይህንን ተከትሎ በኢንዱስትሪ ዘርፍ ተጨባጭ ውጤት እየተመዘገበ መሆኑንም ተናግረዋል።

መንግስት ኢንዱስትሪዎች የሚያጋጥማቸውን ችግር ለመፍታት የአምራች ኢንዱስትሪ ምክርቤት በማቋቋም እየሰራ እንደሚገኝም ጨምረው ገልጸዋል።


የኦሮሚያ መሬት ቢሮ ኃላፊ መሰረት አሰፋ እንዳሉት ቢሮው ከኢንቨስትመንት ቢሮ ጋር በቅንጅት ኢንቨስተሮች በክልሉ ኢንቨስት እንዲያደርጉ ምቹ አስራር ተዘርግቷል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.