የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ

በባሕርዳር ከተማ የኮሪደር ልማትን ጨምሮ የሌሎችም ትላልቅ ፕሮጀክቶች ግንባታ ተጠናክሮ ቀጥሏል

Jun 4, 2025

IDOPRESS

ባሕርዳር፤ ግንቦት26/2017(ኢዜአ)፡- በባሕርዳር ከተማ የኮሪደር ልማትን ጨምሮ የሌሎችም ትላልቅ ፕሮጀክቶች ግንባታ ባለሃብቱንና ሌላውንም ማህበረሰብ በማስተባበር ተጠናክሮ መቀጠሉን የከተማው ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ጎሹ እንዳላማው ገለጹ።

በከተማው እየተከናውኑ በሚገኙ ዋና ዋና ፕሮጀክቶች አፈፃፀም ዙሪያ በየደረጃው የሚገኙ አመራር አባላት የተሳተፉበት የምክክር መድረክ እየተካሄደ ነው።


በመድረኩ ላይ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባው እንዳሉት ፤ በባሕር ዳር ከተማ ሰፋፊና በውጤታማነት የቀጠሉ የተለያዩ የልማት ስራዎች በመከናወን ላይ ይገኛል።

እነዚህም በከተማው የነዋሪዎችን የልማት ፍላጎት እና የከተማዋን ዘላቂ እድገት መሰረት በማድረግ የኮሪደር ልማትን ጨምሮ ሌሎችንም ታላላቅ የመሰረተ ልማት ፕሮጀክቶች እንደሆኑ ጠቅሰዋል።

የልማት ስራዎቹ ነዋሪዎችንና ባለሃብቱን በማሳተፍ የበለጠ ተጠናክረው እንደቀጠሉ ገልጸው፤ ይህንን ይበልጥ በውጤታማነት ለማስቀጠል ገቢ የመሰብሰብ አቅም ማጎልበት እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የከተማ አስተዳደሩ ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ ሃላፊ አቶ ተሻገር አዳሙ በበኩላቸው፤ በከተማው በመጀመሪያውና በሁለተኛው ምዕራፍ 22 ነጥብ 5 ኪሎ ሜትር የኮሪደር ልማት ስራ ለማከናወን ታቅዶ እየተተገበረ እንደሚገኝ ተናግረዋል።


ዕቅዱን ለማሳካት ርብርብ እየተደረገ መሆኑን አስረድተዋል።

እንዲሁም ደረጃቸውን የጠበቁ የአስፋልት መንገዶች ግንባታ ስራ እየተከናወነ እንደሚገኝ አንስተው፤ የልማት ስራዎቹ የከተማዋን እድገት የሚያፋጥኑ እንደሆኑ አስረድተዋል።

በተለይም ከተማዋን ከጣና ሀይቅ ጋር ቀጥታ በማገናኘት ለጎብኝዎችም ሆነ ለነዋሪዎች ይበልጥ ምቹ እያደረገ መሆኑን አብራርተዋል።

ለልማት ስራዎቹ ባለሀብቶች ፣ ነጋዴዎችና ሌሎችም ነዋሪዎች አስተዋጽኦ ማድረጋቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ መልዕክት አስተላለፈዋል።

በመድረኩ የክልል ፣ የከተማ አስተዳደሩና የክፍለ ከተሞች አመራር አባላት እየተሳተፉ ነው።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.