
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 13/2017(ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ለዘላቂና ሁሉን አቀፍ የልማት ስራዎች የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል የተባበሩት መንግስታት ድርጅት(ተመድ) አስታወቀ።
ተመድ በኢትዮጵያ የተለያዩ ዘላቂ የልማት ስራዎችን መደገፍ የሚያስችል የስድስት ነጥብ አምስት ቢሊዮን ዶላር የድጋፍ ስምምነት አድርጓል።
ስምምነቱን የተመድ ረዳት ዋና ጸሀፊ እንዲሁም በኢትዮጵያ የሰብዓዊ ድጋፍ አስተባባሪ ዶክተር ራሚዝ አላካባሮቭ እና የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ ሰመሪታ ሰዋሰው ፈርመውታል።
ስምምነቱ ኢትዮጵያ ቀጣይነት ያለውና ሁሉን አቀፍ ልማት ለማረጋገጥ የምታደርገውን ጥረት የመደገፍ ዓላማ እንዳለው ተገልጿል።
ለአምስት አመት በሚተገበረው ስምምነት በኢትዮጵያ ኢኮኖሚን ለማሳደግ፣ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ፣ ለኢነርጂ ልማት፣ ለትምህርት፣ ለአየር ንብረት ለውጥ መከላከል እና ለሌሎች ዘርፎች እንደሚውልም ተመላክቷል።
የተመድ ረዳት ዋና ጸሀፊ እንዲሁም በኢትዮጵያ የሰብዓዊ ድጋፍ አስተባባሪ ዶክተር ራሚዝ አላካባሮቭ በወቅቱ እንደገለጹት ድጋፉ የኢትዮጵያ የልማት ስራዎችን ለማገዝ ያስችላል።
በቀጣይም ተመድ በኢትዮጵያ ለሚከናወኑ የልማት ስራዎች የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።
የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ ሰመሪታ ሰዋሰው በበኩላቸው፤ የትብብር ስምምነቱ ኢትዮጵያ ለምታከናውናቸው የልማት ስራዎች ወሳኝ መሆኑን አንስተዋል።
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት እያደረገ ላለው ድጋፍ ምስጋና አቅርበው፤ ለስምምነቱ ውጤታማነት በትኩረት ይሰራል ብለዋል።
ባሕርዳር፤ ጳግሜ 5/ 2018 (ኢዜአ) ፡-የሀገርን ቀጣይ ተስፋ እና የትውልዱን እጣ ፋንታ የተሻለ ለማድረግ የዛሬው ብርታትና ትጋታችን ወሳኝ ነው ሲሉ የአማራ ...
Sep 11, 2026
ወላይታ ሶዶ፤ ጳጉሜን 4/2018 (ኢዜአ) ፦በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ለዘመን መለወጫ በዓል የምርት አቅርቦት እጥረት እንዳይከሰት በቂ ዝግጅት መደረጉን የክልሉ ን...
Sep 10, 2026
ባህር ዳር፤ ጳጉሜን 1/2018 (ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የግብርናውን ዘርፍ ከአምራች ኢንዱስትሪው ጋር በማስተሳሰር ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ መቻሉን የክልሉ ...
Sep 7, 2026
ጋምቤላ፤ ነሐሴ 24/2018 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ለአሳ አጥማጆች የተደረገው የግብአት ድጋፍ አበረታች ውጤት እያስገኘ መሆኑን የክልሉ እንስሳትና ዓሳ ሃ...
Aug 31, 2026