
አዲስ አበባ፤ሰኔ 16/2017 (ኢዜአ)፦የግልገል ጊቤ ሦስት ኃይል ማመንጫ ግድብ በዚህ ዓመት 7 ሺህ ጊጋ ዋት ሰዓት ከፍተኛ የኤሌክትሪክ ኃይል በማመንጨት ለኢኮኖሚው እንቅስቃሴ መሳለጥ ጉልህ ሚና መወጣቱን የኃይል ማመንጫ ግድቡ ሥራ አስኪያጅ ሃብታሙ ሰሙ ገለጹ።
ኬንያን ጨምሮ ለቀጣናው ሀገራት የኤሌክትሪክ ኃይል በማቅረብም ትልቅ ሚና እያበረከተ መሆኑን ተናግረዋል።
የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ግድቡ የታዳሽ ኃይልን በማሳደግና የበካይ ጋዝ ልቀትን በመቀነስ ለአረንጓዴ ኢኮኖሚ ግንባታ ጉልህ አስተዋጽኦ እያበረከተ ይገኛል።
የግልገል ጊቤ ሦስት የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ግድብ ሥራ አስኪያጅ ሀብታሙ ሰሙ፥ ግድቡ በ2009 ዓ.ም ተጠናቅቆ አገልግሎት መጀመሩን አውስተዋል።

በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት ላይ ከፍተኛውን ድርሻ በመያዝ ለሀገሪቱ ኢኮኖሚ አዎንታዊ ሚና እየተወጣ የሚገኝ ግዙፉ ፕሮጀክት መሆኑን ገልጸዋል።
ግድቡ 1 ሺህ 870 ሜጋ ዋት ኤሌክትሪክ የማመንጨት አቅም ያለው ሲሆን ከታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ቀጥሎ ግዙፉ የኃይል ማመንጫ መሆኑን ተናግረዋል።
የግልገል ጊቤ ሦስት ኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ግድብ የሀገሪቱን የኃይል አቅርቦት 50 በመቶ በመሸፈን ለጎረቤት ሀገራትም ኃይል በማቅረብ ከፍተኛ ሚና እየተወጣ ነው ብለዋል።
የኃይል ማመንጫ ግድቡ የሥራ ሂደትም በኢትዮጵያውያን ብቁ ባለሙያዎች እየተመራ እንደሚገኝ አብራርተዋል።

ግልገል ጊቤ ሦስት እያደገ ለሚገኘው ሀገራዊ የኤሌክትሪክ ፍላጎት ምላሽ በመስጠት ረገድ ትልቅ አስተዋፅኦ እያበረከተ መሆኑንም ጠቅሰዋል።

በዚህ ዓመትም 7 ሺህ ጊጋ ዋት ሰዓት ኃይል በማመንጨት ለኢኮኖሚ እንቅስቃሴው ጉልህ ሚና እየተጫወተ ነው ብለዋል።
ባህር ዳር፤ ሰኔ 2/2018(ኢዜአ)፦ በአማራ ክልል የማዕድን ሀብት ልማት ዘርፉ በጥናትና ምርምር በመታገዙ ለበርካታ ዜጎች የስራ እድል እየፈጠረና ከፍተኛ የገቢ...
Jun 10, 2026
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 1/2018 (ኢዜአ)፦ ህዝባችን ለአገልግሎት ፍለጋ ጊዜና ገንዘቡን ሳያባክን ሃብቱን ለልማት እንዲያውል የምናደርገውን ጥረት አጠናክረን እንቀጥ...
Jun 9, 2026
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 19/2018 (ኢዜአ)፦ የነገሌ ቦረና ገዳ አውሮፕላን ማረፊያ መመረቅ ፍትሐዊና ሚዛናዊ የመሠረተ ልማት ዝርጋታን የሚያረጋግጥ መሆኑን ጠቅላ...
May 28, 2026
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 11/2018 (ኢዜአ)፡- ቱሪዝም የኢኮኖሚያችን አንዱ ምሰሶ እንደመሆኑ የሀገራዊ ዕድገታችንን የወደፊት አቅጣጫ እየቀረጸ ያለ ዘርፍ መሆኑ...
Apr 20, 2026