
ሆሳዕና ፤ ሰኔ 18/2017(ኢዜአ)፡- በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በግብርናው ዘርፍ እየተመዘገቡ ያሉ ተስፋ ሰጪ ስኬቶችን የማስቀጠሉ ተግባር በተቀናጀ መንገድ እንደሚጠናከር የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶር) ገለጹ፡፡
"የግብርና ሴክተር ምሶሶዎችን በማሳካት የበለፀገ ቤተሰብ ለማየት እተጋለሁ" በሚል መሪ ሀሳብ በግብርና ትራንስፎርሜሽን አቅጣጫዎች ዙሪያ ለግብርና ልማት ሰራተኞች የተዘጋጀ ስልጠና በሆሳዕና ከተማ ተሰጥቷል፡፡

የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው (ዶር) በወቅቱ እንደተናገሩት፤ የሀገር ኢኮኖሚን ለማሳደግ ትኩረት ከተሰጣቸው አምስት ዘርፎች መካከል አንደኛው ግብርና ነው፡፡
ግብርናን ለማዘመን የቴክኖሎጂ አጠቃቀምን በማሳደግ ምርትና ምርታማነትን መጨመር ላይ ትኩረት ተሰጥቶታል ብለዋል፡፡
የግብርናው ዘርፍ ሁሉን አቀፍ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ ያለው አስተዋጽኦ ከፍተኛ ስለመሆኑ ጠቁመዋል፡፡
በክልሉ ቀደም ሲል በተከናወኑ የግብርና ልማት ስራዎች ተስፋ ሰጪ ስኬቶች እየተመዘገቡ መሆናቸውን አንስተው፤የበለጠ ለማጠናከር በተቀናጀ መንገድ እንደሚሰራ ገልጸዋል፡፡

ለዚህም ክልሉ ያለውን መሬት በወቅት ሳይገደብ በአግባቡ በማልማት ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ የግብርና ልማት ባለሙያው ሚና ከፍተኛ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የገጠር ልማት ክላስተር አስተባባሪና የግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ኡስማን ስሩር በበኩላቸው፤ የግብርና ዘርፍ ከድህነት የመውጫ መንገዳችን ነው ብለዋል፡፡

በክልሉ በግብርናው ዘርፍ የተመዘገቡ ስኬቶች እንዲጠናከሩ በትኩረት እንደሚሰራ ገልጸዋል፡፡
በስልጠናው ከሀድያ ዞን የተውጣጡ የግብርና ባለሙያዎች ተሳትፈዋል፡፡
ባሕርዳር፤ ጳግሜ 5/ 2018 (ኢዜአ) ፡-የሀገርን ቀጣይ ተስፋ እና የትውልዱን እጣ ፋንታ የተሻለ ለማድረግ የዛሬው ብርታትና ትጋታችን ወሳኝ ነው ሲሉ የአማራ ...
Sep 11, 2026
ወላይታ ሶዶ፤ ጳጉሜን 4/2018 (ኢዜአ) ፦በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ለዘመን መለወጫ በዓል የምርት አቅርቦት እጥረት እንዳይከሰት በቂ ዝግጅት መደረጉን የክልሉ ን...
Sep 10, 2026
ባህር ዳር፤ ጳጉሜን 1/2018 (ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የግብርናውን ዘርፍ ከአምራች ኢንዱስትሪው ጋር በማስተሳሰር ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ መቻሉን የክልሉ ...
Sep 7, 2026
ጋምቤላ፤ ነሐሴ 24/2018 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ለአሳ አጥማጆች የተደረገው የግብአት ድጋፍ አበረታች ውጤት እያስገኘ መሆኑን የክልሉ እንስሳትና ዓሳ ሃ...
Aug 31, 2026