አሶሳ፤ ሐምሌ 20/2017 (ኢዜአ)፦ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በቴክኖሎጂ የታገዘ የፍርድ አሰጣጥ ሂደት ተግባራዊ መደረጉን የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት አቶ ሰንበታ ቀጄላ ተናገሩ።
የክልሉ ምክርቤት ጉባዔ በሁለተኛ ቀን ውሎው የክልሉን ጠቅላይ ፍርድ ቤት የ2017 በጀት ዓመት ሪፖርት በማድመጥ ላይ ነው።
ሪፖርቱን ያቀረቡት የጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ፕሬዚዳንት ሰንበታ ቀጄላ እንደተናገሩት፤ ተገልጋዮች የተቀላጠፈ አገልግሎት እንዲያገኙ ለማስቻል ችሎቶችን በቴክኖሎጂ በመታገዝ በማከናወን ላይ መሆኑን ጠቅሰዋል።
በዚህም 57 ባለጉዳዮች ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ባዘጋጀው የቪዲዮ ኮንፈረንስ በርቀት የሙግት ክርክር እንዲያገኙ መደረጉን ለአብነት አንስተዋል።
መዝገቦችን ከብልሽት ለመታደግም ወደ ሶፍት ኮፒ የመቀየር ስራ መጀመሩን የተናገሩት ፕሬዝዳንቱ፤ ይህም የፍርድ ቤቱን የውሳኔ ጥራት የሚያሳድግ እና ከተገልጋዮችም አመኔታን የሚያስገኝ ነው ብለዋል።
አክለውም በተጠናቀቀው በጀት ዓመት በክልሉ 18ሺህ 405 መዛግብት የፍርድ ውሳኔ ማግኘታቸውን ገልጸዋል።
ፍርድ ቤቱ ከዳኝነት አገልግሎት 12 ሚሊዮን 813 ሺህ ብር ገቢ ማግኘቱንም ፕሬዝዳንቱ ገልጸዋል።
ምክር ቤቱ በትናንትናው ዕለት የክልሉን አስፈፃሚ ተቋማት እና የምክር ቤቱን ሪፖርት መርምሮ ያፀደቀ ሲሆን በዛሬው ዕለት ደግሞ የክልሉን ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት ሪፖርት፣ የክልሉ የመንግስት ሰራተኞች አዋጅ እና ሌሎች አጀንዳዎች ላይ እንደሚመክር ይጠበቃል።
Jul 17, 2025
Apr 24, 2025
አዲስ አበባ፤የካቲት 4/2017(ኢዜአ)፦ የሲሚንቶ ንግድ እና መሰረታዊ የፍጆታ እቃዎችን በተመለከተ የወጡ መመሪያዎች ገበያውን በማረጋጋትና የዋጋ ግሽበትን በመቀ...
Feb 12, 2025