🔇Unmute
ደሴ ፤ ጥቅምት 1/2018 (ኢዜአ)፡-በደሴ ከተማ የቱሪስት መዳረሻ ሥፍራዎችን በማልማት ለቱሪስቶች ምቹ የማድረግ ተግባር በስፋት እየተከናወነ መሆኑን የከተማ አስተዳደሩ ባህልና ቱሪዝም መምሪያ አስታወቀ።
በደሴ ከተማ "ቱሪዝም ለዘላቂ ልማት" በሚል መሪ ሀሳብ የዓለም የቱሪዝም ቀን ለ33ኛ ጊዜ በተለያዩ ዝግጅቶች ተከብሯል።

የመምሪያው ኃላፊ ወይዘሮ ትዕግስት አበበ በዝግጅቱ ላይ እንደገለፁት፣ በከተማው የቱሪስት መዳረሻ ሥፍራዎችን በማልማት ለቱሪስቶች ምቹ የማድረግ ተግባር በስፋት እየተከናወነ ነው።

በዚህም የደሴ ሙዚዬምን በማደስ፣ የአይጠየፍ አዳራሽ እና የመርሆ ቤተ መንግስታትን ለጎብኚዎች ምቹ በማድረግ ዘርፉ እንዲነቃቃ የማድረግ ስራ መሰራቱን ገልጸዋል።
ለዚህምየቱሪስቶችና የጎብኝዎች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ መምጣቱንና የቆይታ ጊዜያቸውን በማራዘም ውጤት እየተገኘ መሆኑን አስረድተዋል።

የወሎን የአብሮነት፣ የመቻቻል፣ የፍቅርና የሰላም ተምሳሌትነት በተግባር በማሳየት ወሎን የማስተዋወቅ ስራ እየተሰራ እንደሚገኝ ገልጸዋል።
በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የደሴ ከተማ አስተዳደር ጤና መምሪያ ኃላፊ አቶ ሰይድ የሱፍ በበኩላቸው በከተማው የሚገኙ የቱሪስት መዳረሻ ሥፍራዎችን በማልማት የቱሪዝም ዘርፉን ለማነቃቃት እየተሰራ ነው።

አሁን ላይ ባለ 5 ኮከብ እና ዘመናዊ ሆቴሎች፣ የእንግዳ ማረፊያዎችና ሌሎች የአገልግሎት መስጫ ተቋማት እየተገነቡ መሆኑን አስረድተዋል።
በቱሪዝም ቀን አከባበር ስነ ስርዓቱ ላይ አመራሮች፣ የቱሪዝም ባለሙያዎችና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል።
Jul 17, 2025
Apr 24, 2025
አዲስ አበባ፤የካቲት 4/2017(ኢዜአ)፦ የሲሚንቶ ንግድ እና መሰረታዊ የፍጆታ እቃዎችን በተመለከተ የወጡ መመሪያዎች ገበያውን በማረጋጋትና የዋጋ ግሽበትን በመቀ...
Feb 12, 2025