🔇Unmute
አዲስ አበባ፤ጥቅምት 2/2018(ኢዜአ)፦በተቀናጀ የግብርና ልማት ንቅናቄ ምርታማነትን በማሳደግ የኢትዮጵያን ማንሰራራት ለማፋጠን እየተሰራ መሆኑን በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የገጠር ልማት ክላስተር አስተባባሪና የክልሉ ግብርና ቢሮ ሃላፊ አቶ ኡስማን ሱሩር ገለጹ።
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ግብርና ቢሮ የ2017 አፈጻጸም ማጠቃለያ ጉባኤ እና የ2018 የበጋ ወቅት የተቀናጀ የግብርና ስራዎች ንቅናቄ መድረክ በዱራሜ ከተማ እያካሄደ ይገኛል።

በመድረኩ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)፣ የግብርና ሚኒስትር ዴኤታ መለስ መኮንን (ዶ/ር)፣ በምክትል ርዕሰ መስተዳደር ማዕረግ የገጠር ልማት ክላስተር አስተባባሪና የክልሉ ግብርና ቢሮ ሃላፊ አቶ ኡስማን ሱሩርን ጨምሮ የፌደራል እና የክልሉ ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል።
የተቀናጀ የግብርና ልማት ጥረት ለሀገርዊ ማንሰራራት ወሣኝ መሆኑም ተጠቁሟል።
በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የገጠር ልማት ክላስተር አስተባባሪና የክልሉ ግብርና ቢሮ ሃላፊ አቶ ኡስማን ሱሩር በዚሁ ወቅት፤ ከሀገራዊ ለውጡ ወዲህ በግብርናው ዘርፍ የህዝብን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ የቻሉ ስራዎች መሠራታቸውን ተናግረዋል።
ግብርና ለኢኮኖሚ ግንባታ እና ለሀገራዊ ማንሰራራት ስኬታማነት የበኩሉን እያበረከተ እንደሚገኝ ገልጸዋል።
በክልሉ ግብርናን ለማዘመን ብሎም የተነደፉ ኢኒሼቲቮች ስኬታማ እንዲሆኑ ከፍተኛ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ ባለው ስራ የአርሶ አደሩ ተጠቃሚነት እያደገ መመጥቱን ተናግረዋል።

በክልሉ የግብርና ቴክኖሎጂዎችን ከመጠቀም አንጻር መሻሻሎች እየታዩ መሆኑን አንስተው ምርታማነትን ከማሳደግ አንጻርም ውጤቶች መታየት መጀመራቸውን ጠቁመዋል።
ግብርናን በማዘመን የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ ብሎም በዘርፉ የኢትዮጵያን ማንሠራራት ዕውን ለማድረግ በልዩ ትኩረት እየተሰራ ይገኛል ብለዋል።
በ2018 በተቀናጀ የግብርና ልማት ንቅናቄም ምርታማነትን በማሳደግ የኢትዮጵያን ማንሰራራት ለማፋጠን እንደሚሰራም ጠቁመዋል።
በመድረኩም በ2017 በግብርናው ዘርፍ የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ አርሶ አደሮች፣ ወጣቶች፣ ሴቶች እና ባለሃብቶች እውቅና እንደሚሰጡም ተገልጿል።
Jul 17, 2025
Apr 24, 2025
አዲስ አበባ፤የካቲት 4/2017(ኢዜአ)፦ የሲሚንቶ ንግድ እና መሰረታዊ የፍጆታ እቃዎችን በተመለከተ የወጡ መመሪያዎች ገበያውን በማረጋጋትና የዋጋ ግሽበትን በመቀ...
Feb 12, 2025