🔇Unmute
ወላይታ ሶዶ ፤ ጥቅምት 4/2018(ኢዜአ):-በወላይታ ሶዶ ከተማ አርሶ አደሮች ተደራጅተው በእንስሳትና መኖ ልማት የጀመሩት ሥራ ተሞክሮ የሚወሰድበት ነው ሲሉ የተለያዩ ክልሎች የዘርፉ ባለሙያዎች ተናገሩ።
በከተማው ስር የሚገኙ አርሶ አደሮች በመንደር ተደራጅተው በእንስሳትና መኖ ልማት የጀመሩት ሥራ የሌማት ትሩፋት ኢንሼቲቭን የሚያጠናክር መሆኑም ተመልክቷል።
የግብርና ሚኒስቴር ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ግብርና ቢሮ ጋር በመተባበር የእንስሳትና ዓሣ ሀብት ኤክስቴንሽን ምርጥ ተሞክሮን ለመቅሰም ያለመ ሀገራዊ የልምድ መለዋወጫ የመስክ ጉብኝት አካሂዷል።
በመስክ ጉብኝቱ ላይ የተሳተፉት የተለያዩ ክልሎች የዘርፉ ባለሙያዎች እንደገለጹት፣ በከተማው አርሶ አደሮች በመንደር ተደራጅተው በእንስሳትና መኖ ልማት የጀመሩት ሥራ ውጤታማና በአርአያነት የሚወሰድ መሆኑን ተናግረዋል።

አስተያየታቸውን ለኢዜአ ከሰጡ ባለሙያዎች መካከል በአማራ ክልል ግብርና ቢሮ የእንስሳት ሀብት ልማት ባለሙያ አቶ ጌትነት አየሁ እንደገለጹት በከተማው የወተት መንደርን በመፍጠር አርሶ አደሮችን ተጠቃሚ ለማድረግ የተሰራው ሥራ የሚደነቅ ነው።
በተለይ በእንስሳት መኖ ልማት ዘርፍ ያዩትን ተሞክሮ ወደክልላቸው ወስደው በማስፋት የአርሶ አደሮችን ህይወት ለመቀየር እንደሚሰሩ ገልጸዋል።
በኦሮሚያ ክልል ግብርና ቢሮ የእንስሳት ሀብት ልማት ባለሙያ መሠረት ከበደ በበኩላቸው በመስክ ጉብኝቱ ላይ ለሌሎች አርሶ አደሮች ተሞክሮ የሚሆን ልምድ መቅሰማቸውን ተናግረዋል።

በወላይታ ሶዶ ከተማ አርሶ አደሮች በመንደር ተደራጅተው በእንስሳትና መኖ ልማት የጀመሩት ሥራ በሌማት ትሩፋት ኢንሼቲቭ አተገባበር ላይ ተጨባጭ ለውጥ ማምጣቱን አንስተው ይህም ተሞክሮ ማስፋት እንደሚገባም አመልክተዋል።
የመስክ ጉብኝቱ የተሻለ ልምድ ለማግኘት አስችሎናል ያሉት ደግሞ በጎፋ ዞን ግብርና መምሪያ የእንስሳት እና ዓሣ ሀብት ልማት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ሙሉቀን ተመስገን ናቸው።

የወተት ልማትን ከመኖ ልማት ለይቶ ማየት እንደማይቻል ጠቁመው፣ በአንድ አርሶ አደር ከ2 ነጥብ 5 ሄክታር በላይ የመኖ ሣር እየለማ ማየታቸው ለስራው የተሰጠውን ትኩረት ያሳያል ብለዋል።
የእንስሳት እርባታ ሥራው ሳይንሱን የተከተለ መሆኑ ደግሞ አርሶ አደሩን ይብልጥ ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ተናግረዋል።
Jul 17, 2025
Apr 24, 2025
አዲስ አበባ፤የካቲት 4/2017(ኢዜአ)፦ የሲሚንቶ ንግድ እና መሰረታዊ የፍጆታ እቃዎችን በተመለከተ የወጡ መመሪያዎች ገበያውን በማረጋጋትና የዋጋ ግሽበትን በመቀ...
Feb 12, 2025