🔇Unmute
ባሕርዳር ፤ ጥቅምት 4/2018 (ኢዜአ)፡- በአማራ ክልል ከ2 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር በላይ በጀት በመመደብ የመንገድ ግንባታና ጥገና ስራዎች ለማከናወን ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የክልሉ ገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ አስታወቀ።
በክልሉ በተያዘው በጀት ዓመት የመንገድ መሰረተ ልማት ስራዎችን በማከናወን የልማት ትስስሩንና የህዝቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እየተሰራ ይገኛል።
የአማራ ክልል ገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ቀለሙ ሙሉነህ በተለይ ለኢዜአ እንደገለጹት፤ በተያዘው በጀት ዓመት በ34 ፕሮጀክቶች ከ102 ኪሎ ሜትር በላይ የአዳዲስ መንገዶች ግንባታ እንዲሁም የ6 ሺህ 38 ኪሎ ሜትር የነባር መንገዶች ጥገና ለማድረግ ታቅዷል።
ለዚህም ከክልሉ 1 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር እና ከፌዴራል መንገድ ፈንድ አስተዳደር ጽህፈት ቤት ደግሞ ከ1 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር በላይ በጀት ተይዞ የመንገድ ግንባታ ስራዎች ለማከናወን ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል።
በመንገድ ግንባታው የ91 አነስተኛ፣ መካከለኛና ከፍተኛ ድልድዮች ግንባታ የሚካሄድ መሆኑን ጠቁመው፤ መሰረተ ልማቱ ዞን፣ወረዳና ቀበሌዎችን የሚያገናኝ ይሆናል ብለዋል።
በግንባታው ከ20 ሺህ 200 በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የስራ ዕድል የሚፈጥር መሆኑን ገልጸዋል።
Jul 17, 2025
Apr 24, 2025
አዲስ አበባ፤የካቲት 4/2017(ኢዜአ)፦ የሲሚንቶ ንግድ እና መሰረታዊ የፍጆታ እቃዎችን በተመለከተ የወጡ መመሪያዎች ገበያውን በማረጋጋትና የዋጋ ግሽበትን በመቀ...
Feb 12, 2025