🔇Unmute
አምቦ፤ጥቅምት 6/2018(ኢዜአ) ፡- በምዕራብ ሸዋ ዞን በመኸሩ ከ31 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት ላይ ለምቶ የደረሰ ሰብል በመሰብሰብ ላይ መሆኑን የዞኑ ግብርና ጽህፈት ቤት አስታወቀ።
በጽህፈት ቤቱ የአፈር ልማት ማሻሻያ ቡድን መሪ አቶ ተክሌ ኢዶሳ ለኢዜአ በሰጡት ማብራሪያ የመኸሩ የግብርና ልማት በጥሩ ሁኔታ ላይ በመሆኑ የተሻለ ምርት የሚጠበቅበት ነው ብለዋል።

በዞኑ 31 ሺህ 28 ሄክታር መሬት ላይ የለማውና የደረሰው ሰብል አሁን በመሰብሰብ ላይ መሆኑን አንስተው ከዚህም ከ938 ሺህ 490 ኩንታል በላይ ምርት እንደሚጠበቅ ተናግረዋል።
በመኸሩ የስንዴ፣ ገብስ፣ ባቄላ፣ ቦሎቄና ሌሎችም ሰብሎች በመድረሳቸው በመሰብሰብ ላይ መሆናቸውን ገልጸው ከሰብል ስብሰባው ጎን ለጎን የአፈሩን እርጥበት በመጠቀም ዳግም የማልማት የዝግጅት ስራ የተጀመረባቸው አካባቢዎች አሉ ብለዋል።
የመኸር ምርቱ በተሰበሰበባቸው አካባቢዎችም እስካሁን ከ6 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በተለያዩ ሰብሎች የመሸፈን ስራ መከናወኑን ገልጸዋል።
የተሰበሰበውን ሰብል ማሳ እርጥበቱ ሳይጠፋ ዳግም በዘር የመሸፈን ስራው ውጤታማ እንዲሆን ዘመናዊ ማረሻዎች ተሰራጭተው ጥቅም ላይ እንዲውሉ መደረጉንም አስረድተዋል።
Jul 17, 2025
Apr 24, 2025
አዲስ አበባ፤የካቲት 4/2017(ኢዜአ)፦ የሲሚንቶ ንግድ እና መሰረታዊ የፍጆታ እቃዎችን በተመለከተ የወጡ መመሪያዎች ገበያውን በማረጋጋትና የዋጋ ግሽበትን በመቀ...
Feb 12, 2025