🔇Unmute
ሰመራ፤ ጥቅምት 12/2018(ኢዜአ)፦ የክልሉን እምቅ የእንስሳትና ዓሳ ሃብት ልማት በማዘመን የዘርፉን ተጠቃሚነት ለማሳደግ የተቀናጀ ጥረት እየተደረገ መሆኑንየአፋር ክልል የእንስሳትና ዓሳ ሀብት ልማት ቢሮ አስታወቀ።
"በሌማት ትሩፋት መርሃ ግብር ትግበራ ክልሉን የቤተሰብ ብልፅግና ተምሳሌት ማድረግ" በሚል መሪ ሐሳብ የአፋር ክልል እንስሳትና ዓሳ ሃብት ልማት ቢሮ እና ተጠሪ ተቋማቱ በሠመራ ከተማ የምክክር መድረክ አካሂደዋል።

የአፋር ክልል እንስሳትና ዓሳ ሃብት ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ኢብራሂም መሐመድ፤ የክልሉን እምቅ የእንስሳትና ዓሳ ሃብት ልማት በማዘመን የዘርፉን ተጠቃሚነት ለማሳደግ የተቀናጀ ጥረት እየተደረገ መሆኑን ገልጸዋል።
የዘርፉን ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ በማሳደግ የአርብቶ አደሩን የምግብ ዋስትና ለማረጋገጥ ባለፉት የለውጥ ዓመታት ብዙ ስራዎች መሰራታቸውን አስታውሰው በተለይም የሌማት ትሩፋት መርሃ ግብር ብዙዎችን ተጠቃሚ እያደረገ ይገኛል ብለዋል።
በመርሃ ግብሩ የስጋ፣ የወተት፣ የእንቁላልና የማር ምርቶችን ከፍ ማድረግ መቻሉን ገልፀው፤ በዓሳ ሃብትም በተመሣሣይ ለውጦች መመዝገባቸውን ነው ያብራሩት።
የዘርፉን ስኬት ለማጉላት የደረቅ መኖ ዝግጅት ላይ በማተኮር መሰራቱን ሲያነሱ ለአብነትም ባለፈው ዓመት 362 ሺህ ቶን የእንስሳት መኖ ማምረት መቻሉን አብራርተዋል።
በዚህም ባለፉት አምስት ዓመታት በመኖ ዝግጅት ዘርፍ 46 ሺህ አርብቶ አደሮችን ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን ገልጸዋል።
በቢሮው የእንስሳት ጤና አገልግሎትና ኢንስፔክሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አብዱልቃድር መሐመድ በበኩላቸው በክልሉ ውስጥ ካሉ ሀብቶች አንዱና ዋነኛው የእንስሳት ሀብት መሆኑን ጠቁመዋል።

የእንስሳቱን ጤንነት በማስጠበቅ ምርታማነታቸውን ለማሳደግ ከአጋር አካላት ጋር መሰራቱን ተናግረዋል።
Jul 17, 2025
Apr 24, 2025
አዲስ አበባ፤የካቲት 4/2017(ኢዜአ)፦ የሲሚንቶ ንግድ እና መሰረታዊ የፍጆታ እቃዎችን በተመለከተ የወጡ መመሪያዎች ገበያውን በማረጋጋትና የዋጋ ግሽበትን በመቀ...
Feb 12, 2025