🔇Unmute
ክልል፤ ጥቅምት 21/2018 (ኢዜአ)፡- በኦሮሚያ ክልል በተያዘው በጀት ዓመት የመጀመሪያው ሩብ አመት ገበያ ለማረጋጋት በተቀናጀ አግባብ በተሰራ ስራ ውጤት እየተገኘ መሆኑን የክልሉ ንግድ ቢሮ አስታወቀ።
የኦሮሚያ ክልል ንግድ ቢሮ ምክትል ሀላፊ አቶ ተስፋዬ ገሾ ለኢዜአ እንደተናገሩት በበጀት አመቱ በክልሉ ገበያን ለማረጋጋት አቅርቦትን መጨመርና የቁጥጥርና የክትትል ስራ ተጠናክሮ ቀጥሏል።
በሩብ ዓመቱም ቢሮው ህገ ወጥ ንግድ መከላከል ላይ ያተኮረ የግንዛቤ ማሳደጊያ ስራ መስራቱን ተናግረዋል።
ህገ ወጥ ንግድን ከመከላከል ጎን ለጎን የምርት ተደራሽነት እንዲሰፋ በማድረግ አቅርቦት እና ፍላጎት እንዲጣጣም ሲሰራ መቆየቱንም አስታውሰዋል።

በዚህም የግብርና ምርቶችንና ለምግብነት የሚውሉ የኢንዱስትሪ ውጤቶችን በብዛት፣ በጥራትና በተመጣጣኝ ዋጋ በቅዳሜና እሁድ ገበያ፣ በባዛርና በኤግዚቢሽን ለህብረተሰቡ እንዲቀርብ መደረጉን ነው የተናገሩት።
እንዲሁም ከባለ ድርሻ አካላት፣ ከዩኒየኖች፣ ከህብረት ስራ ማህበራትና በከተማ ግብርና ላይ ከተሰማሩ አካላት ጋር በመሆን የተሻሉ የአቅርቦት ስራዎች መሰራታቸውን ተናግረዋል።

በክልሉ ባለፉት ሶስት ወራት 19 ተጨማሪ የቅዳሜና እሁድ ገበያዎችን በማቋቋም በአጠቃላይ ወደ 590 ገበያዎች ማድረስ መቻሉን ጠቅሰው በነዚህ አማራጭ ገበያዎች የፍጆታ ምርቶች እንዲቀርቡ በማድረግ ገበያ ማረጋጋት መቻሉን አንስተዋል።
በተለይም የአትክልትና ፍራፍሬ አምራቾች በአቅራቢያቸው በተፈጠረ የገበያ ትስስር ምርቶችን ለህብረተሰቡ ተደራሽ እያደረጉ በተሻለ መልኩ ተጠቃሚ መሆናቸውን ተናግረዋል።

እንዲሁም በክልሉ ከሚገኙ የምግብና ምግብ ነክ አምራች ኢንዱስትሪዎች ህብረተሰቡ በፋብሪካ ዋጋ ምርት እንዲያገኝ መደረጉን አንስተዋል።
Jul 17, 2025
Apr 24, 2025
አዲስ አበባ፤የካቲት 4/2017(ኢዜአ)፦ የሲሚንቶ ንግድ እና መሰረታዊ የፍጆታ እቃዎችን በተመለከተ የወጡ መመሪያዎች ገበያውን በማረጋጋትና የዋጋ ግሽበትን በመቀ...
Feb 12, 2025