🔇Unmute
ሰመራ፣ጥቅምት 28/2018(ኢዜአ) ፡- በአፋር ክልል ሰመራ ሎጊያ ከተማ የሚካሄደውን የከተሞች ፎረም ማስተናገድ የሚያስችሉ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች መጠናቀቃቸውን የከተማ አስተዳደሩ አስታወቀ።
የኢትዮጵያ የከተሞች ፎረም መካሄድ ከተሞችን እርስበርስ ለማስተዋወቅ፣ በከተሞች መካከል የውድድርና የፉክክር መንፈስ እንዲጎለብት በማድረግ የከተሞችን የልማት ጉዞ ለማፋጠን መነሳሳት እንደሚፈጥር ተመልክቷል።
በተጨማሪም በከተሞች ለቱሪዝም የሚውሉ ታሪካዊ፣ ባህላዊና ማህበራዊ እሴቶች ለማስተዋወቅም ፎረሙ ጉልህ ድርሻ አለው ተብሏል።
ሰመራ ሎጊያ ከተማ “የከተሞች ዕድገት ለኢትዮጵያ ልህቀት" በሚል መሪ ሐሳብ የሚካሄደው 10ኛውን የኢትዮጵያ የከተሞች ፎረም ታስተናግዳለች።
በዚሁ ጉዳይ ላይ ከኢዜአ ጋር ቆይታ ያደረጉት የሰመራ ሎጊያ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አብዱ ሙሳ እንደገለፁት ፎረሙ ሰመራን እና አጠቃላይ በአፋር ክልል ያለውን ተፈጥሯዊና ታሪካዊ ሀብቶችን ለማያስተዋውቅ የሚያግዝ ነው።
ሰመራ ለዝግጅቱ ድምቀት ዘርፈ ብዙ የዝግጅት ስራዎች መከናወናቸውን ገልጸው በተለይም 6 ሺህ ካሬ ላይ ያረፈ ለዐውደ ርዕይ እና ለሌሎች አገልግሎት የሚውል ስፍራ የዝግጅቱ አንድ አካል መሆኑን ተናግረዋል።
ስፍራው ለዐውደ ርዕይ የሚሆን ሼድ፣ ውሃ፣ መብራት፣ ስልክና የገመድ አልባ ኢንተርኔት እንዲያገኝ ተደርጓል ነው ያሉት።
በዘንድሮው የከተሞች ፎረም ላይ የሚሳተፉ 148 ከተሞች ምርቶቻቸውን የሚያሳዩበት ስፍራም መዘጋጀቱን ገልጸዋል።
ከህዳር 6 እሰከ 10 ቀን 2018 ዓ.ም ባሉት ተከታታይ ቀናት በተለያዩ ዝግጅቶች እንደሚካሄድ አመልክተው የፎረሙ መክፈቻ እና መዝጊያ ሁነቶች የሚካሄዱበት የሰመራ ስታዲዮም እና ሌሎች ሁነቶች የሚስተናገዱበት የተለያዩ የስብሰባ አዳራሾች መዘጋጀታቸውን ገልጸዋል።
ከከተሞች ፎረም ጎን ለጎን በከተማው የተሰሩ የኮሪደር ልማት፣ የልማት ስራዎችና የተፈጥሮ መስህብ መዳረሻ ቦታዎች ጉብኝት እንደሚደረግም ታውቋል።
በፎረሙ ላይ ከዐውደ ርዕይና ሌሎች ሁነቶች በተጨማሪ በተለያዩ መስኮች ጥናታዊ ፅሁፎች እንደሚቀርቡና በከተማ ልማት ፖሊሲ ዙሪያ ውይይት እንደሚደረግ ይጠበቃል።
ባሕርዳር፤ ጳግሜ 5/ 2018 (ኢዜአ) ፡-የሀገርን ቀጣይ ተስፋ እና የትውልዱን እጣ ፋንታ የተሻለ ለማድረግ የዛሬው ብርታትና ትጋታችን ወሳኝ ነው ሲሉ የአማራ ...
Sep 11, 2026
ወላይታ ሶዶ፤ ጳጉሜን 4/2018 (ኢዜአ) ፦በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ለዘመን መለወጫ በዓል የምርት አቅርቦት እጥረት እንዳይከሰት በቂ ዝግጅት መደረጉን የክልሉ ን...
Sep 10, 2026
ባህር ዳር፤ ጳጉሜን 1/2018 (ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የግብርናውን ዘርፍ ከአምራች ኢንዱስትሪው ጋር በማስተሳሰር ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ መቻሉን የክልሉ ...
Sep 7, 2026
ጋምቤላ፤ ነሐሴ 24/2018 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ለአሳ አጥማጆች የተደረገው የግብአት ድጋፍ አበረታች ውጤት እያስገኘ መሆኑን የክልሉ እንስሳትና ዓሳ ሃ...
Aug 31, 2026