🔇Unmute
አዲስ አበባ፤ ሕዳር 10/2018(ኢዜአ)፦ የሱዳን ግጭት ዘላቂ መፍትሄ እንዲያገኝ ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ የተቀናጀ ምላሽ እንዲሰጥ የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን (ኢጋድ) ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር) ጥሪ አቀረቡ።
የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን (ኢጋድ) ያዘጋጀው ሁለተኛ የሱዳን የልዩ ልዑኮች ፎረም ዛሬ በጅቡቲ ተካሄዷል።
በፎረሙ ላይ የኢጋድ ዋና ፀሐፊ ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር)፣ ቀጣናዊ እና ዓለም አቀፍ ተዋንያን ተሳትፈዋል።
ፎረሙ በሱዳን ላለው ቀውስ የተቀናጀ መልስ መስጠት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ያተኮረ ነው።

የኢጋድ ዋና ፀሐፊ ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር) በፎረሙ መክፈቻ ላይ ባደረጉት ንግግር የሱዳን ሰላም በሱዳናውያን የሚመራ፣ ቀጣናዊ ትብብር የተረጋገጠበት እና ዓለም በአንድ ድምጽ የሚደግፈው ሊሆን እንደሚገባ አመልክተዋል።
በሱዳን ያለውን ግጭት ለማስቆም፣ ንጹሃን ዜጎችን ለመጠበቅ እና የኢጋድ ቀጣናን የተረጋጋ ለማድረግ በቅንጅት መስራት እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል።
ዋና ፀሐፊው ኢጋድ ከአፍሪካ ህብረት እና ዓለም አቀፍ አጋሮች ጋር በመሆን በሱዳን የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ እንዲደረስ፣ የሰብዓዊ እርዳታ መተላለፊያ እንዲከፈት እና ተአማኒነት ያለው የስልጣን ሽግግር እንዲኖር በቁርጠኝነት ይሰራል ብለዋል።
ኢጋድ ሱዳናውያን በሀገራቸው ሰላም እና ደህንነት እንዲረጋገጥ እንዲሁም ክብራቸው እንዲጠበቅ ያላቸው መሻት እንዲሳካ አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ በመረጃው አመልክቷል።
Jul 17, 2025
Apr 24, 2025
አዲስ አበባ፤የካቲት 4/2017(ኢዜአ)፦ የሲሚንቶ ንግድ እና መሰረታዊ የፍጆታ እቃዎችን በተመለከተ የወጡ መመሪያዎች ገበያውን በማረጋጋትና የዋጋ ግሽበትን በመቀ...
Feb 12, 2025